ከ--- እስከ የተሰኘ መጽሃፍ ለንባብ በቃ

Wednesday, 14 February 2018 12:38

 

በይርጋ አበበ

ትኩረቱን ፍቅር ላይ ያደረገው የወጣቷ ደራሲ ሂክመት አብዱ የመጀመሪያ ስራ የሆነው “ከ…. እስከ” ልብ ወለድ መጽሃፍ ለንባብ በቅቷል።


በ87.99 ብር ዋጋ ለኢትዮጵያዊያን አንባቢዎች ለገበያ የቀረበው ይኸው መጽሃፍ ህትመቱን ፋር ኢስት ትሬዲንግ ነው የሰራው። ከ… እስከ በ184 ገጾች የተዘጋጀ ሲሆን 25 ንዑስ ርዕሶችን የያዘ መጽሃፍ ነው። ከኢትዮጵያ ውጭ ለሚገኙ የመጽሃፉ ፈላጊዎች መሸጫ ዋጋው 20 የአሜሪካ ዶላር ነው።


ጸሃፊዋ የስነ ልቦና ምሩቅ ስትሆን የከፍተኛ ትምህርቷን በምትከታተልበት ወቅት ገና የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እያለች መጻፍ እንደጀመረች ለሰንደቅ ጋዜጣ ተናግራለች። ይህም ማለት መጽሃፉን አዘጋጅቶ ለማጠናቀቅ ከአምስት ዓመት ያላነሰ ጊዜ እንደወሰደባትም ጨምራ ተናግራለች።


መጽሃፉን ገዝተው ማንበብ ለሚሹ መሸጫ ቦታዎቹ በሁሉም መጽሃፍ አዟሪዎች እና በጃፋር፣ በዩኒቨርሳል፣ በእነሆ መጽሃፍ እና ሌሎች መጽሃፍ መደብሮች በኩል መሆኑን ከደራሲዋ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
493 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 127 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us