11ዱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በብሔራዊ መግባባት ላይ ለመደራደር ረቂቅ አዘጋጅተው አቀረቡ

Wednesday, 21 March 2018 12:43

 

በይርጋ አበበ

 

በኢህአዴግ እና በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል እየተካሄደ ባለው ድርድር አስራ አንዱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከኢህአዴግ ጋር በብሔራዊ መግባባት ዙሪያ ለመደራደር ረቂቅ አዘጋጅተው ማቅረባቸው ተገለጸ፡


የኢዴፓ ሊቀመንበር ዶክተር ደጫኔ ከበደ እና የመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለጹት ፓርቲዎቹ የመደራደሪያ ረቂቅ ሰነዱን ያስገቡት ትናንት ማክሰኞ ነው። ለድርድር ከቀረቡ ነጥቦች መካከል ብሔራዊ መግባባት በ12ኛ ደረጃ የተቀመጠ ቢሆንም ቀሪ ነጥቦች ለድርድር ከመቅረባቸው በፊት በብሔራዊ መግባባት ላይ ቅድሚያ ሰጥተው መደራደር እንደሚፈልጉ ባስታወቁት መሰረት ኢህአዴግ ጥያቄውን ተቀብሎ ለድርድር መዘጋጀቱን የሁለቱ ፓርቲዎች መሪዎች አስታውቀዋል።


እንደ ሁለቱ ፖለቲከኞች አስተያየት የብሔራዊ መግባባትን ወደ ፊት መጥቶ ለድርድር የቀረበው አሁን አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ ነው። በዚህ ዙሪያም ቀደም ሲል ከኢህአዴግ መሪዎች ጋር የተናጠል ውይይት ማድረጋቸውን የገለጹት መሪዎቹ፤ ኢህአዴግ መጀመሪያ ጥያቄውን ለመቀበል ፈቃደኛ ባይሆንም ከወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳያ አኳያ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ጫና ማሳደራቸውን ተናግረዋል። በዚህም ሁሉን አቀፍ አሳታፊ የውይይት መድረክ እንዲመቻች የሚያስችል ረቂቅ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።


በተያያዘ ዜና ከዚህ ቀደም በአራተኛው መደራደሪያ ነጥብ ማለትም በጸረ ሽብር ህጉ ማሻሻያ ዙሪያ ድርድር ከመካሄዱ በፊት ኢህአዴግ ሃሳቡን ባለማቅረቡ እስካሁን ድርድር ሳይካሄድ መቆየቱን የመኢአድና የኢዴፓ መሪዎች ገልጸዋል። ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ከቀረበለት የማሻሻያ ረቂቅ በኋላ የራሱን ሃሳብ ባለማቅረቡ መግባባት ላይ ሳይደርሱ መቆየታቸውን የገለጹት የሁለቱ ፓርቲ መሪዎች፤ በመጨረሻም ኢህአዴግ ረቂቅ ሃሳቡን በባለሙያ ለማስጠናት በጠየቀው መሰረት ጊዜ እንደተሰጠው ገልጸዋል። በዚህም ከወር በላይ ድርድር ሳይካሄድ መቅረቱን አስታውሰዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1910 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 186 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us