የአሜሪካ ግዙፍ ኩባንያዎች ትራምፕ ከቻይና ጋር ያለው የሁለትዮሽ ንግድ እንዳይረብሹ አሳሰቡ

Wednesday, 21 March 2018 12:49

 

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ በአውሮፓና በቻይና የብረትና የአልሙኒየም ምርቶች ላይ ታሪፍ ለመጣል የያዙትን አቋም ተከትሎ የአሜሪካ ንግድ ምክር ቤት አባላት ስጋታቸውን ገልፀዋል።

አባላቱ ፕሬዝዳንቱ ሊወስዱት ያሰቡትን እርምጃ ተከትሎ በተለይ ከቻይና በኩል ሊኖር የሚችለው አፀፋዊ ምላሽ አጠቃላይ የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነቱን ሊረብሸው ይችላል በማለት ነው ሥጋታቸውን የገለፁት። ብሉምበርግ ባሰራጨው ዘገባ እንዳመለከተው ይህንን ሥጋታቸውን በአፅዕኖት የገለፁት የአሜሪካ የንግድ ምክርቤትና ሌሎች 44 ከንግድ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ማህበራት ናቸው።

እነዚህ የንግድ አካላት ግዙፎቹን አፕል፣ ጎግል እና ዎልማርትን ጭምር የሚያካትቱ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ ያመለክታል። ከንግድ ግንኙነት ጋር በተያያዘ አሜሪካ በቻይና ላይ ቅሬታን ከማቅረብ ባለፈ እርምጃ ለመውሰድ ስትንደረደር ይህ የመጀሪያዋ ባይሆንም እስከዛሬም ድረስ ይህ ነው የሚባል ወሳኝ እርምጃ የወሰደችበት ሁኔታ አልነበረም።

ቻይና በተለይ የሌሎች ሀገራትን ተመሳሳይ ምርቶች ከገበያ ውጪ በማድረግ በመጨረሻ ገበያውን በበላይነት ለመቆጣጠር ያስችላት ዘንድ የተደጎሙ ምርቶችን ኤክስፖርት ታደርጋለች በሚል በርካቶች ቅሬታቸውን ያሰሙባታል። ይህ ብቻ ሳይሆን ጥራት የጎደላቸው ምርቶችን ወደ ገበያ ታስገባለች እንደዚሁም የአሜሪካዊያንን አዕምሯዊ ንብረቶችን ሳይቀር ያለ ፈቃድ አባዝታ ጥቅም ላይ ታውላለች በሚል ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል።

ችግሮቹ ባለፉት ፕሬዝዳንቶች አስተዳደሮች ወቅት በተደጋጋሚ ሲሰሙ ቢቆዩም ይህ ነው የሚባል ወጥነት ያለው የሁለትዮሽ መግባባት ላይ ግን መድረስ የተቻለበት ሁኔታ አልነበረም። ሆኖም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጉዳዩን ጠበቅ አድርገው በመያዝ ወደ ተግባር ለመግባት የሚያስችሏቸውን ሥራዎች እየሰሩ መሆኑን ዘገባዎች እያመለከቱ ነው።

ሁኔታው ጠንከር እያለ በመጣበት በአሁኑ ሰዓት ግን የትራምፕን እርምጃ ተከትሎ ቻይና ልትወስድው በምትችለው አፀፋዊ እርምጃ የንግድ እንቅስቃሴያቸው እንዳይጎዳ ሥጋቱ ያደረባቸው የአሜሪካ ግዙፍ ኩባንያዎች ትራምፕን መማፀንን መርጠዋል። የትራምፕ አስተዳደር በጉዳዩ በደንብ ሲያስብበት ከቆየ በኋላ ከሁሉም በፊት ወደ አሜሪካ በሚገቡ በቻይና የብረትና የአልሙኒየም ምርቶች ላይ 25 እና 10 በመቶ ታሪፍ ለመጣል ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን የቀደሙ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ግዙፎቹ የአሜሪካ ኩባንያዎች በንግድ ምክርቤታቸው በኩል ለትራምፕ በፃፉት ደብዳቤ እርምጃቸው አጠቃላይ የንግድ ስርዓቱን ከመረበሽ ባሻገር በተጠቃሚዎች ላይ የዋጋ ንረት የሚያስከትል መሆኑን ገልፀዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን ምርቶቻቸውን ወደ ቻይና በሚልኩ አሜሪካዊያን ኩባንያዎች ላይም የቻይና የአፀፋ እርምጃ የሚያርፍ ከሆነ የአሜሪካንን ኢኮኖሚ መልሶ መጉዳቱ አይቀርም የሚል ሥጋትንም ኩባንያዎቹ ያነሱ መሆኑን የብሉምበርግ ዘገባ ጨምሮ ያመለክታል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1948 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 973 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us