ግብፅና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ተስማማን እያሉ ነው

Wednesday, 21 March 2018 12:45

 

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከሰሞኑ በካይሮ ቆይታ ያደረጉ ሲሆን በጉብኝቱ ማጠናቀቂያ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የህዳሴው ግድብ ሊያደርሰው በሚችለው ተፅዕኖ ዙሪያ ሁኔታውን መቋቋም ይቻል ዘንድ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ያመለከቱ መሆኑን ዘገባዎች አመልክተዋል። መሪዎቹ በዚሁ የጋራ መግለጫቸው “በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችን ጋር በጋራ እንሰራለን” በማለት የተናገሩ መሆኑን የግብፅ ደይሊ ኒውስ ዘገባ ያመለክታል።


ሱዳን ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ግልፅ ድጋፍ መስጠቷን ተከትሎ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የሻከረበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። ከዚህና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ግብፅ የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ ከሶስትዮሽ ድርድሩ እንድትወጣና ጉዳዩ የኢትዮጵያና የግብፅ ጉዳይ ብቻ እንዲሆን ለማድረግ የራሷን ያልተሳካ ጥረት ስትሞክር ቆይታለች። የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሲወጣና ሲወርድ የቆየ ሲሆን ውጥረቱን ለማርገብም የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካይሮ መሰንበታቸውን የቀደሙ ዘገባዎች ያመለክታሉ። የሱዳኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የካይሮ ቆይታ መጠናቀቅ ተከትሎ ወደ ካይሮ ያመሩት አልበሽር ከግብፅ ጋር በኢነርጂ፣ በትራንስፖርትና በሌሎች የመሰረተ ልማት ዘርፎች ሀገራቸውን ለማስተሳሰር በበርካታ የልማት ጉዳዮች ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የግብፅ ደይሊ ኒውስ ዘገባ ያመለክታል።


የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከህዳሴው ግድብ ባሻገር ሱዳን ለቱርክ የጦር ሰፈር ልትሰጥ ነው በሚልና በግዛት ይገባኛል ጥያቄ ውጥረት ውስጥ መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን እነዚህን የውጥረት ምንጮች በተመለከተ በዚህ ጉብኝት የተባለ ነገር የለም።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
2038 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 929 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us