ኦህዴድ ወጣቶች ጥያቄያቸውን በሰከነ መንፈስና በታላቅ ሃገራዊ ስሜት እንዲያቀርቡ ጥሪ አቀረበ

Wednesday, 28 March 2018 12:13

 

28ኛው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የምስረታ በዓል ድርጅቱ ለክልሉ እና ለሀገሪቱ ህዝቦች ብልፅግና ዳግም ቃሉን የሚያድስበት እንደሚሆን የማዕከላዊ ኮሚቴው ፅህፈት ቤት ሰሞኑን አስታውቋል።


ፅህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ ኦህዴድ ፌደራላዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የጣሉ ተግባራትን ለመፍታት ከህዝቡ እና የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ጋር በመሆን በፅናት እንደሚታገል አስታውቋል። መግለጫው ኦህዴድ በሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ትግል ተጸንሶ ለሰፊው ህዝብ መብትና ጥቅም ከህዝብ አብራክ የተወለደ ህዝባዊ ድርጅት መሆኑን ጠቅሷል።


ኦህዴድ በርካታ ክልላዊና ሃገራዊ ተልዕኮዎች መወጣቱን ያነሳው መግለጫው፥ ድህነትን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ለክልሉና ለሃገሪቱ የህዳሴ ጉዞ ስኬት አኩሪ ተግባር እያከናወነ ነው ብሏል። ድርጅቱ ለህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና ዘላቂ ልማት መረጋገጥ ቁርጠኛ ነው ያለው መግለጫው፥ የምስረታ በዓሉ ኦህዴድ ለመስመሩ ቀጣይነትና ለሃገሪቱ ህዝቦች ብልጽግና ዳግም ቃሉን የሚያድስበት መሆኑንም አንስቷል።


ኦህዴድም እንደ ከዚህ ቀደሙ ለክልሉና ለሃገሪቱ የህዳሴ ጉዞ ስኬት እና ለህዝቦች አብሮነትና አንድነት የሚያደርገውን ትግል ከመቸውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል መግለጫው። ድርጅቱ ሚሊየን ወጣቶችን ሚሊየነር ለማድረግ በሚል መርህ የስራ አጥነት ችግርን በመቅረፍ ስራ ፈጣሪ ዜጋን ማፍራት ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎ እየሰራ መሆኑም በመግለጫው ተነስቷል።


ወጣቶችም በስራዎች ሂደት ላይ ለሚኖራቸው ማንኛውም ጥያቄ ሃገር የመረከብ ሃላፊነት በእነርሱ ላይ የወደቀ መሆኑን በመገንዘብ በሰከነ መንፈስና በታላቅ ሃገራዊ ስሜት እንዲንቀሳቀሱም ጠይቋል። የኦሮሞ ምሁራንም ሃገራቸውንና ክልላቸውን እውቀት በማምጣት እንዲገነቡም ጥሪውን አቅርቧል።


መግለጫው የኢህአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች አሁን በተደረሰበት የትግል ምዕራፍ ተገምግመው የተቀመጡ ሃገራዊ አቅጣጫዎች፥ በሚፈለገው ፍጥነት በመተግበር ለሃገሪቱ ህዝቦች መብት መከበርና ለህዳሴው ጉዞ ስኬት ርብርብ እንዲያደርጉም መልዕክቱን አስተላልፏል።


መላው የሃገሪቱ ህዝቦችም ሃገሪቱን ለመገንባት የጋራ እሴቶቻቸውን በማጎልበትና የስኬት ጅማሮዎች ለፍሬ እንዲበቁ እጅ ለእጅ ተያይዘው ለሃገሪቱ የህዳሴ ጉዞ መሳካት በጋራ እንዲሰሩም ጠይቋል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
740 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 187 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us