በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከአንድ ሺህ ህፃናት 29ኙ አንድ ዓመት ሳይሞላቸው ይሞታሉ

Wednesday, 28 March 2018 12:23

በይርጋ አበበ

 

በዓለም ላይ ከፍተኛ የህጻናት ሞት ከሚስተናገድባቸው ስድስት አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ የህፃናት ሞት ቁጥር አሁንም ከፍተኛ መሆኑን በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ዶክተር እንዳለ ዮሴፍ ገለጹ።


ለመገናኛ ብዙሃን ስለ ህጻናት ጉዳይ ዘገባ በተመለከተ ስልጠና በተሰጠበት ወቅት ዶክተር እንዳለ ዮሴፍ እንደገለጹት በኢትዮጵያ በየዓመቱ በህይወት ከሚወለዱ አንድ ሺህ ህጻናት መካከል 29ኙ ይሞታሉ። በክልል ደረጃ ያለውን ለማመልከትም ለአብነት በኦሮሚያ ያለውን አኃዝ ሲገልጹ ከአንድ ሺህ ህጻናት 37ቱ ይሞታሉ ብለዋል።


ዩኒሴፍ በዚህ ጉዳይ ድጋፍ ከሚያደርግላቸው ክልሎች አንዱ በሆነው ኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ‹‹አዳማ ሜዲካል ኮሌጅ ወይም በቀድሞ ስያሜው ኃይለማሪያም ማሞ ሆስፒታል›› ተገኝተን በተመለከትንበት ወቅት በልዩ ሁኔታ የሐኪም ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ህጻናት መርጃ መሳሪያዎች እጥረት እንዳለባቸው የተቋሙ ሐኪሞች ተናግረዋል። በዚህ የተነሳም በቂ ህክምና እና ክትትል ለማድረግ መቸገራቸውን የተናገሩት ሲስተር ትዕግስት ጉተማ በአዳማ ሜዲካል ኮሌጅ ኒዮናታል አይሲዩ ክፍል ኃላፊ፤ “ልዩ ክትትልና ህክምናውን መስጫ መሳሪያዎች እና የባለሙያ እጥረት አለ። በቀን ማስተናገድ የምንችለው 13 ህጻናትን ብቻ ቢሆንም ካለው የታካሚ ብዛት የተነሳ በቀን እስከ 65 ህጻናት ህክምና እንሰጣለን” ያሉ ሲሆን ይህም ለታካሚዎች ተገቢውን ህክምና እንዳያገኙ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ ለሐኪሞቹም ጫና እንደሆነባቸው ገልጸዋል። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
730 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 185 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us