ኖህ ሪል ስቴት ግዙፉን የመኖሪያ ሕንጻ አስመረቀ

Wednesday, 04 April 2018 13:49

ኖህ ሪል ስቴት ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ ያስገነባውን ኖህ ሴንትረም የመኖሪያ ግዙፍ ባለ16 ፎቅ ሕንጻ (አፓርትመንት) ባለፈው እሁድ መጋቢት 23 ቀን 2010 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ቤት የገዙ ደንበኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስመረቀ።

 

የኖህ ሪል ስቴት የሥራ መሪዎች ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት አፓርታማው በጠቅላላው 226 ያህል ባለአንድ፣ ባለሁለትና ባለሶስት መኝታ ቤቶችን የያዘ ሲሆን ባለ አራት ቤዝመንት የመኪና ማቆሚያ ሥፍራ ጨምሮ 10 ሺ ካሬ ሜትር የሚሸፍን የመኪና ማቆሚያ ሥፍራን ያካተተ ነው። በተጨማሪም መብራት በሚቋረጥበት ወቅት መጠባበቂያ ጄኔሬተር፣ ለነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሱፐርማርኬት፣ የሕጻናት መዋያ፣ ጂምናዚየምና የመሳሰሉ አገልግሎት መስጫዎችን ያሟላ ነው።


የሪልስቴት ዘርፉ አንዳንድ ተዋንያን በገቡት ኮንትራት መሠረት ሥራቸውን ካለማከናወናቸው ጋር ተያይዞ በደንበኞች ዘንድ እየተከሰተ ያለውን ያለመተማመን ችግር ለመቅረፍ፤ ኖህ ሪል ስቴት “ያልተገነባ አንሸጥም!” በሚለው መርህ ሥራውን በማከናወን በደንበኞቹ ዘንድ አመኔታ ማትረፍ እንዳስቻለው ተወስቷል።


ከተመሠረተ ስድስት ዓመታትን ያስቆጠረው ኖህ ሪል ስቴት በ600 ሚሊየን ብር ያስገነባውንና አትላስ ሆቴል አካባቢ የሚገኘውን ይህንኑ የመኖሪያ ቤቶች ቁልፍ በዕለቱ ለደንበኞቹ አስረክቧል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
504 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 156 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us