ተስፋ ማተሚያ ቤት ህልውናው አደጋ ላይ ወደቀ

Wednesday, 04 April 2018 13:42

በይርጋ አበበ

 

ከተመሰረተ መቶኛ ዓመቱን ባሳለፍነው ሳምንት ያከበረው ተስፋ ገብረሥላሴ ማተሚያ ቤት በኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ‹‹በቅርስነት›› ቢመዘገብም ህልውናው አደጋ ላይ ወድቋል።


ማተሚያ ቤቱ ህልውናው አደጋ ላይ የወደቀው በአካባቢው የሚሰሩ ግንባታዎች ለማተሚያ ቤቱ ደህንነት አደጋ ስለሆኑበት እና መውጫ እና መግቢያ በር ስላሳጡት መሆኑን የማተሚያ ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥበበ ተስፋ ገብረስላሴ ተናግረዋል።


የማተሚያ ቤቱ ስራ አስኪያጅ እንደገለጹት ተስፋ ገብረስላሴ ማተሚያ ቤት ከ1910 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ የህትመት ስራዎችን ሲያካሂድ የቆየ ቢሆንም መንግስት ማተሚያ ቤቱ የሚገኝበትን አካባቢ (አራት ኪሎ) በመልሶ ማልማት ለህንጻ ግንባታዎች የከለለው ቦታ በመሆኑ ማተሚያ ቤቱ ማንነቱን እንዲያጣ ተደርጓል። የማተሚያ ቤቱ ንብረት የሆነ ሰፊ መሬትም በመልሶ ማልማት ለባለንብረት ስለተላለፈበት የግቢው መጠን አነስተኛ ሆኖበታል። ዙሪያ ገባውን የሚገነቡት ህንጻዎችም ቁፋሮ ሲያካሂዱ የማተሚያ ቤቱን ቅጥር ግቢ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደረጉት ሲሆን በአሮጌ ማሽን የህትመት ስራዎችን ሲያካሂድ የቆየውን ማተሚያ ቤት ስራዎቹን በዘመናዊ ማሽን ለማካሄድ የማተሚያ ማሽን ቢገዛም ወደ ግቢው ለማስገባት ተቸግሯል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
431 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 899 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us