በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የፒዛ ሃት ሬስቶራንት ተከፈተ

Wednesday, 11 April 2018 14:05

በላይ አብ ፉድስ እና ፕሮዳክሽን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር በአዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች የፒዛ ሃት ሬስቶራንቶችን ከፈተ።

 

የአሜሪካ የሬስቶራንት ሰንሰለት የሆነው ፒዛ ሃት በኢትዮጵያ ትልቅ የምግብ ፍራንቻይዝ በመክፈት የመጀመሪያው አለም አቀፍ ድርጅት ሆኗል። ሬስቶራንቶቹ በትናንትናው ዕለት ተመርቀው ሲከፈቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የሆኑት ማይክሌ ሬይነር፤ የYum! Brands Inc. ተወካዮች፤ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


የኢትዮጵያ ፍራንቻይዝ ባለቤት የሆነው በላይ አብ ፉድስ እና ፕሮዳክሽን ኃ.የተ.የግ ማህበር ይህንን ትልቅ ሬስቶራንት የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በማስመጣት በሁለት ቦታዎች ማለትም በሲኤምሲ እና ከፍተኛ እንቅስቃሴ በሚደረግበት በቦሌ መድሃኒዓለም አካባቢ ለመክፈት በቅቷል።


‹‹ይህንን የመሰለ ታሪካዊ ቀን ላይ በመገኘታችን በጣም ደስተኞች ነን›› ይላሉ የበላይ አብ ፉድስ ሼር ሆልደር እና ሲኢኦ አቶ ሚካኤሌ ገብሩ። ቀጥለውም ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የተወሰኑ አህጉራዊ ፋራንቻይዝ ሬስቶራንቶች ቢገኙም፤ ፒዛ ሃት ግን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የገባ የመጀመሪያው አለም አቀፍ መልቲናሽናል የሬስቶራንት ፍራንቻይዝ ነው›› ብለዋል። አክለው ሲናገሩም፤ ‹‹በአሜሪካ ሀገር የሚገኙ የሬስቶራንቱ ፍራንቻይዞች ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች የስራ እድል የሚፈጥሩ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 85 በመቶ ከ25 አመት በታች ናቸው። በላይ አብ ፉድስ ይህንን ባህል በመከተል ወጣቶች ትምህርታቸውን እናዳጠናቀቁ በመቅጠርና የተለያዩ ሀገራት ወስዶ ስልጠና በመስጠት ከፒዛ ሃት ብራንድ ጋር እንዲዋሀዱ አድርጓል›› ብለዋል።


ፒዛ ሃትን ያቀፈው Yum! Brands Inc. በተጨማሪም እና KFC እና Tacobell የመሳሰሉ ብራንዶችን የያዘ ሲሆን በአፍሪካ አህጉር የበለጠ በመስፋፋት ላይ ይገኛል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
509 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 118 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us