ንግድ ሚኒስቴር ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ለመቆጣጠር እየሰራሁኝ ነው አለ

Wednesday, 11 April 2018 14:09

በተለያዩ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ሸማቹ ህብረተሰብ ላይ ጫና ለመፍጠር የሚሞክሩ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የኢፌዲሪ ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

 

በተለይም አብዛኛው ነጋዴ ለሸማቹ የሚያስብ፣ ለሀገር ለውጥ የሚተጋ፣ ማትረፍ በሚገባው ልክ የሚያተርፍ እና የነፃ ገበያ መርህን ተከትሎ የሚሰራ ነው። ሆኖም አንዳንድ ነጋዴዎች የምርቶችን ጥራት በማጓደል እና ከባእድ ነገር በመቀላቀል ለሸማቹ ህብረተሰብ በማቅረብ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘትና ምርቶችን በመሰወር ያለአግባብ ዋጋ በመጨመር ለመጠቀም የሚፈልጉ እንዳሉ የኢፌዲሪ ንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ጠቁመዋል።


በመሆኑም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደ ሀገር የወጪ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያ ከተደረገበት ከጥቅምት 2010 ዓ.ም ጀምሮ ገበያውን ለማረጋጋት ከፌዴራል እስከ ከተማ አስተዳደር፣ ክልል፣ ክፍለ ከተማና ወረዳ ድረስ በተዘረጋው መዋቅር አማካኝነት ክትትል ያደርጋል።


ከአላግባብ ዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ከንግዱ ማህበረሰብ አካላት ጋር በመመካከር፣ በማስተማር፣ በመገሰፅ ከሚገባው በላይ ዋጋ መጨመርና ተገቢ ያልሆነ ትርፍ ማግኘት ሸማቹን የሚጎዳ መሆኑን በማስገንዘብና በውይይት መተማመን ላይ በመድረስ እየተፈታ ነው።


በዚህ ሂደት በተደጋጋሚ የገበያ ህጉን የሚጥሱ፣ የውድድር ስርዓቱን የሚያዛቡና የሸማቹን ጥቅም የሚጎዱ ብሎም በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ለማሳደር ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ጨምረው በተገኙ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው።


ክትትል ከሚደረግባቸው ምርቶች መካከል አንዱ የምግብ እህሎች ሲሆን የውጪ ምንዛሬ ለውጥ ሳይደረግ በፊት የነበረው ዋጋ መነሻ አድርገን አሁን ላይ ያለውን ዋጋ ስናይ ያለው ጭማሪ አነስተኛ ነው። በአንዳድ እህሎች ላይ የቀነሰበት ሁኔታ አለ ይህም በ2009 እና 2010 የመህር ወቅት ምርቱ ከፍተኛ መሆን ዋጋው ባለበት እንዲሄድ አድርጎል።


ሁለተኛው ከአትክልትና ፍራፍሬ መካከል የተወሰነ ለውጥ ያለው በብርቱካን ዋጋ ላይ ሲሆን ሌላው ባለበት ነው ያለው። ይህም ባሳለፍነው ወር አቅርቦቱን ስናይ በጣም ጥሩ የነበር ሲሆን አቅርቦት በደንብ ካለ ገበያውና ሸማቹ እራሱ ዋጋውን እንደሚቆጣጠሩ አቶ ወንድሙ ፍላቴ አስረድተዋል።


ሶስተኛ የአግሮ ኢንዱስትሪ ምርቶች ያለው ዋጋ ሁኔታ ጥሩ ሲሆን አራተኛው የብረታ ብረት ማለትም የግንባታ እቃዎችና የአርማታ ብረታ ብረት በሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች የምርቶቹን ፍላጎት መሸፈን ስለማይቻል ከውጭ ሀገር በማስገባት እየተሰራጨ ነው።


እንደ ሀገር የወጪ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ እነዚህ ምርቶች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል። ይህም በሀገር ደረጃ በሁሉም ቦታዎች ግንባታዎች እየሰፉ መምጣትና የኮንስራትራክሽን ኢንዱስትሪው እያደገ በመምጣቱ የምርቶቹ ፍላጎት አድጓል። በተጨማሪም በዘርፉ ያሉ ነጋዴዎች የውጪ ምንዛሬውን ተመን መሻሻል ምክንያት አድርገው የምርቶቹን ዋጋ በጋራ በመወሰን እና በመጨመር ሰው ሰራሽ የሆነ የዋጋ አለመረጋጋት ፈጥረው ነበር።


በመሆኑም በአንድ በኩል ከእነዚህ አካላት ጋር በተከታታይ መድረክ በመፍጠር ዋጋ የማረጋጋት በሌላ በኩል ደግሞ አቅርቦት እንዲሻሻል የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።


በዓልን ምክንያት በማድረግ ያለተገባ ዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ሲያጋጥሙ ህብረተሰቡ በየደረጃው ለሚገኙ ንግድ ቢሮዎችና ለንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ጥቆማ እንዲያደርግ ኃላፊው ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
512 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1079 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us