የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ሊቀመንበር በእስር ላይ ናቸው

Wednesday, 11 April 2018 14:11

 

የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ መስራችና ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ተሻለ ሰብሮ ለፖሊስ ከሰጡት ቃል ጋር በተያያዘ የስም ማጥፋት ክስ ተመስርቶባቸው በደቡብ ክልል ሆሳዕና ከተማ ትናንት ለሕትመት እስከገባንበት ድረስ ታስረው እንደሚገኙ ተሰማ።

አቶ ተሻለ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ዕለት ጠዋት ጀምሮ የታሰሩት ቀደም ሲል ከቤተሰብ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ቀርቦባቸው ለነበረ ክስ ለፖሊስ በሰጡት ቃል ስማችን ጠፍቷል ያሉ ወገኖች በመሰረቱባቸው ክስ መሆኑን ለሰንደቅ ጋዜጣ ትላንት በስልክ።

“በደረሰኝ መጥሪያ መሠረት ወደሆሳዕና ሌሞ ወረዳ ፖሊስ ሄጄ ቀርቤያለሁ፣ ነገርግን ፖሊስ ፍ/ቤት ዳኞች እስኪሰየሙ ጠብቅ ተብዬ በእስር ላይ እገኛለሁ” ብለዋል።

የታሰሩበትን ምክንያት ሲያስረዱም “ቀደም ሲል በተከሰስኩበት ወቅት ለፖሊስ ቃል ስሰጥ የግለሰቦችን ስም ጠቅሻለሁኝ፤ እነዚያ ግሰለቦች ከፖሊስ ጋር በመመሳጠር በስም ማጥፋት ክስ እንዳቀረቡብኝ ተረድቻለሁ» ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ተሻለ አያይዘውም መቼ ፍ/ቤት እንደሚቀርቡ አለማወቃቸውንም ጠቁመዋል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሕግ ባለሙያ ስለክሱ ጭብጥ ተጠይቀው በሰጡት አስተያየት አንድ ተከሳሽ እንደፖሊስ ላሉ የፍትህ አካላት በሚሰጠው ቃል የስም ማጥፋት ክስ ሊቀርብበት አይችልም። መብቶች ተነጻጻሪ ናቸው ያሉት ባለሙያው አንድ ተከሳሽ ለመከላከል ያስችለኛል የሚለውን ቃል በነጻነት እንደሚሰጥ፣ ፖሊስም ለፍ/ቤት ካልሆነ በስተቀር ሚስጢሩን አሳልፎ መስጠት ከስነምግባር ውጪ መሆኑን ጠቅሰው ክሱ ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል።

በአቶ ተሻለ ሰብሮ የሚመራው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ፤ ከኢህአዴግ ጋር መስርቶት ከነበረው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክክር መድረክ አጀንዳዎች ባለመስማማት ራሱን ማግለሉ የሚታወስ ነው።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
628 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1042 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us