ስለፓርኪንሰን የግንዛቤ ማስጨበጫ የእግር ጉዞ በአዲስ አበባ ተካሄደ

Wednesday, 18 April 2018 12:35

 

በይርጋ አበበ

 

የፓርኪንሰን ህመም በዓለም ላይ ስለ በሽታው እውቅና የተሰጠው ከ200 ዓመታት በላይ ቢያስቆጥርም በኢትዮጵያ ግን ስለ ህመሙ እና ስለ ህሙማኑ በቂ መረጃ ባለመኖሩ ታማሚዎቹ ለከፋ ችግር ተዳርገው ቆይተዋል።

በዚህ የተነሳም በአገር ቤት የመድሃኒት አቅርቦት እና ስርጭት እንዲሁም የዋጋው ከፍተኛ መሆን ታካሚዎችን እንደጎዳቸው ይናገራሉ። ይህን መሰል ውስብስብ ችግር ያለበት ህመም ታማሚዎቹ መድሃኒቱን በቀላሉ አግኝተው ህመማቸውን እንዳይከታተሉ በመንግስት በኩል የተሰራ ስራ አለመኖሩ ችግሩን የከፋ አድርጎት ቆይቷል። ከመንግስት በተጨማሪም በህብረተሰቡ ዘንድ ስለ በሽታው በቂ ግንዛቤ ስለሌለ ታማሚዎቹ ችግራቸውን የሚረዳላቸው የለም።

ባሳለፍነው ቅዳሜ ረፋዱ ላይ መነሻውን ቴዎድሮስ አደባባይ አድርጎ መድረሻውን ኢትዮኩባ አደባባይ ያደረገ የእግር ጉዞ የተካሄደውም ስለ በሽታው በቂ ግንዛቤ ለማዳበር ታስቦ ነው። በዕለቱም በርካታ የህመሙ ተጠቂዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

በዕለቱም ከፓርኪንሰን ህሙማን ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን ጋር አብረው ለሰሩ ድርጅቶች የምስጋና እና የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው ሲሆን ህመሙን በተመለከተም በጤና ባለሙያዎች፣ በማህበሩ አምባሳደር ተዋናይ ደሳለኝ ክብረት እና በታማሚዎች ሰፊ ገለጻ ተደርጓል። ፓርኪንሰን በሁሉም የዕድሜ ክልል የጾታ ልዩነት ሳያደርግ ሁሉንም ሰው የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን የእጅ እና የእግር እንቅስቃሴ እንዲሁም የአንደበትን ተግባር የሚገታ ከባድ በሽታ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ምን ያህል ሰዎች በዚህ በሽታ እንደተጠቁ የተደረገ ጥናት የለም።

ፓርኪንሰን ህመም የታማሚን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚገታ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በዚህ ህመም ከተጠቁት ታዋቂ ሰዎች መካከል አሜሪካዊው ቦክሰኛ መሀመድ አሊ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር የነበሩት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ይገኙባል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
230 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 69 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us