የኢትዮጵያ ፌዴራዝም ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ብሔርተኝነት እንዲጎላ አድርጓል ተባለ

Wednesday, 18 April 2018 12:35


በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ መንግስት የሚከተለው ፌዴራላዊ የመንግስት ስርዓት በኢትዮጵያዊነት አንድነት ላይ አሉታዊ ሚና መጫወቱ ተገለጸ።

በፌዴራሊዝም ስርዓት ሁለንተናዊ ይዘት ላይ ትናንት በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በተካሄደ የውይይት መድረክ እንደተገለጸው በዚህ ወቅት ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ብሔርተኝነት ጎልቶ ተገኝቷል። ይህ የሆነው ደግሞ ፌዴራሊዝሙን መንግስት የተገበረበት መንገድ ስህተት በመሆኑ ለውይይቱ የመነሻ ሃሳብ ጥናት ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፌዴራሊዝም ትምህርት አስተማሪው ዶክተር አሰፋ ፍሰሃ ተናግረዋል። ፌዴራሊዝሙ ከኢትዮጵያዊነት እና ከማዕከላዊ መንግስቱ ይልቅ ለክልሎች የሰጠው ስልጣን ከፍተኛ መሆኑን ምሁሩ ጨምረው ተናግረዋል።

በዚህ ወቅት አካባቢያዊነት መንገሱ ከተሳታፊዎች የተነሳ ሲሆን፤ በቅርቡ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል የተፈጠረው ግጭትም አንዱ የአካባቢያዊነት ስሜት ጎልቶ መውጣት ምሳሌ መሆኑን ዶክተር አሰፋ ተናግረዋል። ኢትዮጵያዊነት እንዲጎለብት ተቋማት አልተጠናከሩም እንዲሁም አገራዊ እሴት የለም ሲሉ ተሳታፊዎች ገልጸዋል። የውይይት መድረኩን ያዘጋጀው የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ነው።

ኢትዮጵያ ከአሃዳዊ የመንግስት ስርዓት ወደ ፌዴራላዊ የመንግስት ስርዓት የተሸጋገረቸው በ1983 ዓ.ም ከተካሄደው የስርዓት ለውጥ በኋላ ነው።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
280 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 188 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us