በሞያሌ የቦምብ ጥቃት ደረሰ

Wednesday, 18 April 2018 12:55

በሞያሌ ቦምብ ጥቃት በዜጎች ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደረሰ፡፡ በትላንትናው ዕለት በደረሰው የእጅ ቦምብ ጥቃት 3 ንፁኃን ዜጎች ህይወታቸው ያለፈ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ አንዳንድ ዘገባዎች ከእጅ ቦንቡ መወርወር በሶማሌ እና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል ቀደም ብሎ ግጭቶች የተከሰቱበት ሁኔታዎች እንደነበሩ ያመለክታሉ፡፡ ከተገደሉት 3 ሰዎች በተጨማሪ 63 የሚሆኑ ዜጎች የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

በቅርቡ በሞያሌ ከተማ በፀጥታ ኃይሎች በስህተት ተፈፀመ በተባለ ግድያ በርካታ ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ደንበር አቋርጠው ወደ ሞያሌ የተሰደዱበት ሁኔታ ነበር፡፡ ከመንግስት በኩል ይወጡ የነበሩ መረጃዎች ከግድያው በኋላ በከተማዋ የታየውን አንፃራዊ መረጋጋት ተከትሎ በርካቶች ወደ ከተሰደዱበት ወደ መኖሪያ ቀያቸው እየተመለሱ ያሉበት ሁኔታ ነበር፡፡ የአሁኑ የቦምብ ጥቃት በአካባቢው በድጋሜ አለመረጋቱ እንዳያገረሽ ሥጋትን አሳድሯል፡፡

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
340 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 66 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us