ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ይመረቃል

Wednesday, 18 April 2018 12:38

-    ዩኒቨርሲቲውን የሚያስመርቀው የዞኑ ህዝብ ነው

 

በሰሜን ጎንደር ዞን ዋና ከተማ በሆነችውና ከአዲስ አበባ 830 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ደባርቅ ከተማ የተከፈተው አዲሱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ በተለያዩ ዝግጅቶች ይመረቃል። ዩኒቨርሲቲው በሀገራችን ብዙም ባልተለመደ ሁኔታ የዞኑ ህዝብ የሚያስመርቀው መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል።

በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የሚኖረው ህዝብ በነፍስ ወከፍ የተሳተፈበት ይህ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የምረቃ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች የሚታጀብ ሲሆን የአካባቢው ተወላጅ የሆኑትን ታላቁን የስፖርት ሰው የኢንስትራክተር እንዳልክ ቀለመወርቅ መታሰቢያ የሆነው ከሊማሊሞ አናት የሚነሳ የጎዳና ላይ ሩጫ የዝግጅቱ አንድ አካል ነው።

በደባርቅ የአንድ ቀን የቱሪዝምና ኢንቨስትመንት ፎረም የተዘጋጀ ሲሆን አካባቢውን የሚያስተዋውቅ አውደ ርዕይም ዩኒቨርሲቲውን ለማስመረቅ ከተዘጋጁ ኩነቶች አንዱ ነው።

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 8 ቀን 2007 ዓ.ም በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የመሰረተ ድንጋዩ ተቀምጦ ከ452 ሚሊዮን ብር በላይ ለመነሻ ግንባታው በተፈቀደው በጀት ግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ.ም ግንባታው ተጀምሮ ታህሳስ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ ተጠናቋል። በአሁኑ ወቅት ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ 1ሺህ 175 ተማሪዎችን ተቀብሎ በተለያዩ የትምህርት መስኮች እያስተማረ ይገኛል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
389 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 219 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us