ከመመሪያ ውጪ ሲሰሩ በተገኙ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

Wednesday, 25 April 2018 12:16

ከመመሪያ ውጪ ሲሰሩ ተገኝተዋል በተባሉ የንግድ ተቋማት በአስመጪና እና በላኪነት የንገድ ዘርፍ የተሰማሩ 178 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ንግድ ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት 737 የንግድ ተቋማት ላይ የድህረ ፈቃድ ክትትልና ቁጥጥር አድርጓል፡፡ በተደረገውም ክትትልና ቁጥጥር ከመመሪያ ውጪ ሲሰሩ በተገኙ የንግድ ተቋማት ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊና የእርምት እርጃዎችን ወስዷል፡፡

በንግድ ሚኒስቴር የድህረፈቃድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት የውጪ ኢንስፔክሽን ቡድን መሪ ወ/ሮ መአዛ ውቤ እንደተናገሩት በ13 ተቋማት ላይ የጹሁፍ በ 162ቱ ላይ የቃል ማስጠንቀቂያ እንዲሁም በ3 የንግድ ተቋማት ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል፡፡

እንደወ/ሮ መአዛ ገለጻ 61 የንግድ ተቋማት በኦዲት ላይ መሆናቸውን 6 ተቋማት ደግሞ በገቢዎችና ጉምሩክ በኩል የታሸጉ መሆናቸውን በክትትልና በቁጥጥሩ ወቅት ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን 80 የንግድ ተቋማት ባስመዘገቡት አድራሻ አልተገኙም፡፡

በድህረ ፈቃድ ቁጥጥሩ ከተደረገባቸው የንግድ ተቋማት ውስጥ በህጉ መሰረት ሲሰሩ የተገኙ 176 ናቸው ሲል የንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
106 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 187 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us