ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከሀይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች ጋር ቅዳሜ ይመክራሉ

Wednesday, 25 April 2018 12:19

በይርጋ አበበ

የቀድሞው ፕሬዝዳት መቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ የፊታችን ቅዳሜ በመኖሪያ ቤታቸው በሚገኘው ‹‹የሰላም አዳራሽ›› ከአገር ሽማግሌዎችና ከሀይማኖት መሪዎች ጋር በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ህዝብ ግንኙነት ዙሪያ ምክክር ያደርጋሉ።

የምክክር መድረክ ያዘጋጀው ሰለብሪቲ ኤቨንትስ የተባለ ድርጅት ሲሆን በዕለቱ መቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኙ የሀይማኖት መሪዎች፣ ምሁራን፣ የአገር ሽማግሌዎች እና ታዋቂ ሰዎች የሚሳተፉ ይሆናል።

ከዚህ ቀደም በተካሄዱ የውይይት መድረኮች ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎች በአብዛኛው የትግራይ ክልል እና የኤርትራ ተወላጆች ናቸው፤ በዚህ ላይ ያልዎት አስተያየት ምንድን ነው? የሚል ለውይይት መድረኩ አዘጋጆች ጥያቄ ቀርቦላቸው በሰጡት ምላሽ “ጥሪ ያቀረብንላቸው ለሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች ቢሆንም እንደተባለው በመጀመሪያዎቹ ውይይቶች ላይ በብዛት ተሳታፊ የነበሩ ሰዎች እንደተባለው ከሁለቱ አካባቢዎች የመጡ ነበሩ። ሆኖም ከቅርብ ጊዜያት በኋላ ግን የውይይት መድረኩን አላማ እየተረዱ ስለመጡ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የመጡ ሰዎች (ምሁራን፣ አርቲስቶች፣ አትሌቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት መሪዎች) የውይይት መድረኩ ተሳታዎች ይሆናሉ” ሲሉ መልሰዋል።

አዘጋጆቹ አክለውም በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግጭት ከሁለት የተከፈሉት ትግራይ ብቻ ሳይሆኑ አፋር፣ ሳሆ (ኢሮብ) እና ኩናማ በሁለቱም በኩል የሚገኙና የችግሩ ገፈት ቀማሽ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የፊታችን ቅዳሜ በሚካሄደው የፓናል ውይይት 100 ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን የሚሳተፉ መሆኑን አዘጋጆቹ ጨምረው ገልጸዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
131 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 183 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us