“አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስር ነቀል ለውጥ እንጂ ጥገናዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስቡ ከሆነ የአገሪቱን ችግር ሊፈቱ አይችሉም”

Wednesday, 25 April 2018 12:23

“አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስር ነቀል ለውጥ እንጂ ጥገናዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስቡ ከሆነ

የአገሪቱን ችግር ሊፈቱ አይችሉም”

አቶ ስዩም ተሾመ

በይርጋ አበበ

በኢትዮጵያ ለተፈጠሩ ችግሮች ዋናው ምክንያት ለዴሞክራሲ መሰረት የሚሆን ስርዓት አለመገንባቱ ነው ሲሉ የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር አቶ ስዩም ተሾመ ገለጹ።

ሰማያዊ ፓርቲ ባሳለፍነው ቅዳሜ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውይይት መነሻ ሃሳብ ያቀረቡት መምህር ስዩም ተሾመ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ችግር የህገ መንግሰቱ አንቀጽ ስምንት ነው። “እናም” ይላሉ አቶ ስዩም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለዚህች አገር ችግር መፍትሔ እሰራለሁ ካሉ የበርካታ ኢትዮጵያዊያንን ህይወት ለቀጠፈው የህገ መንግስት ክፍተት ማሻሻያ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆን አለባቸው    ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ መዋቅር ሲያካሂዱ ሁሉንም ከኢህአዴግ አባል ነው በዚህ ሁኔታ እሳቸውን ለውጥ ያመጣሉ ብሎ መጠበቅ ይቻላል ወይ? የሚል ጥያቄ ከተሳታፊዎች የቀረበላቸው አቶ ስዩም ሲመልሱ፤ “በግልጽ ለመናገር ጥያቄው የተመሰረተው ከጠባቂነት ስሜት ነው። በመሰረቱ ዶክተር አብይን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ያበቃቸውን ለውጥ ያመጣው የተቃዋሚ ፓርቲዎች መታሰርና የህዝብ ቁጣ እንጂ የኢህአዴግ ለለውጥ መዘጋጀት አይደለም። ስለዚህ አዲሱ የኢህአዴግ አመራር ለውጥ ያመጣ ይሆን? ብሎ ከመጠየቅ ከኢህአዴግ ውጭ ያሉት የፖለቲካ ሀይሎች ምን እያደረጉ ነው? ብሎ መጠየቅ ያሻል። ከዚህ አንጻር ሲታይ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ እዚህ ግባ የሚባል ስራ እያደረጉ ነው ማለት አይቻልም” ሲሉ ተናግረዋል።

ኢህአዴግ በ1994 ዓ.ም ባወጣው ፖሊሲ እና ስትራቴጂ “ዋና ጠላታችን ድህነት ነው” ብሎ መነሳቱና በድህነት ላይ ዘመቻ መክፈቱን ያስታወሱት መምህር ስዩም “በኢህአዴግ ቤት እንደሚባለው 11 በመቶ እድገት ባይመዘገብም የተወሰነ ደረጃ የኢኮኖሚ እድገት ተመዝግቦ ነበር። ሆኖም እድገቱ ቀጣይነቱ ሳይረጋገጥ ባለበት ቆመ፤ እየቆየ ደግሞ ወደኋላ ተመለሰ” ያሉ ሲሆን ይህ የሆነበትን ምክንያት ሲያስቀምጡም ኢህአዴግ ከ1997 ዓ.ም በኋላ የዴሞክራሲ በሮችን ሙሉ በሙሉ በመዝጋቱ እንደሆነ ገልጸዋል። የደቡብ ኮሪያዊያን ከድህነት ወደ ብልጽግና ያደረጉትን የ1950ዎቹን ተሞክሮ አቶ ስዩም አስታውሰዋል። ደቡብ ኮሪያዊያን እድገታቸው ቀጥሎ የሄደው የአገሪቱ ገዥ ፓርቲ ከኢኮኖሚ ችግራቸው በተጨማሪ የዴሞክራሲ ጥያቄያቸው መልስ በሚያገኝበት መልኩ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ስላሰፋ መሆኑን ተናግረዋል።

“አዲሱ የኢህአዴግ አመራር የተቃዋሚዎችን አጀንዳ የቀማ ሳይሆን አጀንዳውን አስፈጻሚ ነው” ያሉት አቶ ስዩም፤ ወደ ስልጣን የመጣውን አዲሱን የኢህአዴግ አመራር ሲገልጹትም ‹‹በኢህአዴግ ውስጥ ሆኖ ምቹ ሁኔታዎችን ሲጠብቅ የነበረ ጥቅመኛ (Opportunist) ነው›› ብለዋል። “ዶክተር አብይን ጨምሮ አዲሶቹ አመራሮች ትክክለኛ ለውጥ ፈላጊ (Reformist) ከሆኑ የአገሪቱን መሰረታዊ ችግር ከስሩ የሚነቅል ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ይኖርባቸዋል” በማለትም ተናግረዋል። እንደ አቶ ስዩም ገለጻ ስር ነቀል ለውጥ የሚሉት የህገ መንግስት ማሻሻያ ማድረግ ነው።

ሰማያዊ ፓርቲ የሚያዘጋጀው ተመሳሳይ ፕሮግራም በየሳምንቱ የሚቀጥል መሆኑን ገልጾ፤ የፊታችን ቅዳሜም ከሰዓት በኋላ አምባሳደር አካባቢ በሚገኘው ጽ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚቀጥል መሆኑን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ አካሉ ለሰንደቅ ጋዜጣ ተናግረዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
171 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 184 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us