የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥትና ኢህሶዴፓ አዳዲስ የካቢኔ ሹመትና ሽግሽግ አጸደቀ

Wednesday, 25 April 2018 12:25

ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባካሄደው ስብሰባ በክልሉ መስሪያቤቶችና በአንዳንድ ዞኖች አዲስ አመራሮች እና የካቢኔ ሹመት መሰየሙን አስታውቋል።

የማዕከላዊ ኮሚቴውን ስብሰባ የመሩት የኢህሶዴፓ ሊቀመንበር አቶ መሀመድ ረሺድ ኢሳቅ እና ም/ሊቀመንበርና የክልሉ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር መሆናቸው ተዘግቧል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው በሰጠው አዳዲስ ሹመቶችና ሽግሽግ መሰረት፤ ወ/ሮ ፈርቱን አብዲ ማህዲ፣ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ፤ አቶ አህመድ አብዲ፣ የውሃ ሀብት ቢሮ ኃላፊና ስራ የኢህሶዴፓ አስፈፃሚ አባል፤ አቶ አብዲሀኪም ኢጋል፣ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ የኢህሶዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፤ ወ/ሮ ሱኣድ አህመድ ፋረህ፣ በነበሩበት (የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ)፤ አቶ ከድር አብዲ ኢስማዕል፣ የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊ፤ አቶ ሀምዲ አደን አብዲ፣ የኢ.ሶ.ክ.መ ም/ፕሬዝዳንትና የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ፤ አቶ ሱልጣን መሀመድ ሀሰን፣ የስራ አስፈፃሚ አባልና የመስኖና ተፋሰስ ልማት ቢሮ ሃላፊ፤ ወ/ሮ ማጂዳ መሀመድ፣ የመስተዳደር ፅ/ቤት ሃላፊ፤ አቶ ኡመር መሀመድ፣ በነበረበት (የኢሶህዴፓ ፖለቲካ ጉዳየች ኃላፊ)፤ አቶ ኢብራህም አሊ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ፤ አቶ ባሼ አብዲ እስማኢል፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክትል ቢሮ ሃላፊ፤ አቶ ፉኣድ ጃማ ወላቢ፣ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ፤ አቶ መሀመድ ረቢዕ ሃጂ አብዲቃድር፣ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ፤ አቶ አብዲላሂ መሀመድ ገርቦ፣ የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ቢሮ ኃላፊ፤ አቶ ሃሩን ዩሱፍ አብዲ ንግድ፣ ትራንስፖርትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ፤ ወ/ሮ ረህማ መሀሙድ፣ በነበሩበት (የሴቶችና ህፃነት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ)

አቶ አብዲመሀድ መሀመድ አባስ፣ እንስሳትና አርብቶኣደር ልማት ቢሮ ኃላፊ፤ አቶ ጀማል ፋረህ ወርሞጌ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ፤ አቶ ኢብራህም አደን መሀድ፣ በነበሩበት (ትምህርት ቢሮ ኃላፊ)፤ አቶ አብዲጀማል አህመድ ቆለንቢ፣ በነበሩበት (ጠቅላይ አቃቢ ህግና ፍትህ ቢሮ ኃላፊ)፤ አቶ ጀማል ኢስማን ቆረኔ፣ የስራ አስፈፃሚ አባል፤ አቶ መሀመድ ቢሌ ሀሰን፣ የቴክኒክ፣ ሞያና ትምህርት ስልጠና ቢሮ ኃላፊና የፕሬዝዳንቱ የሚዲያ ዘርፍ አደካሪ፤ ኢንጅነር አሰድ ኡመር፣ በነበሩበት (የገጠር መንገዶች ልማት ባለስልጣን ኃላፊ)፤ አቶ ረሺድ ጃመእ ሼር ምክትል ቢሮ ኃላፊ፤ አቶ ሀሰን አደን ሀሰን ምክትል ቢሮ ኃላፊ ናቸው።

በተያያዘም በዞን የተሾሙት አመራሮች፤ አቶ አብዲአሲስ አህመድ ሀቢዬ፣ ቀድሞ የሸቤሌይ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩት አሁን የቆረሄይ ዞን አስተዳዳሪ፤ አቶ ሙሐመድ ሀሰን ሱፊ፣ ከደገህቡር ከተማ ከንቲባነት ወደ የጀረር ዞን አስተዳዳሪ፤ አቶ ሀቢብ አደን፣ ከወረዳ አስተዳደሪነት ወደ ዞን አስተዳዳር ኃላፊነት፤ አቶ መሀመድ አሊ፣ የፋፈን ዞን ትምህርት መመሪያ ኃላፊ የነበሩ ወደ የዳዋ ዞን አስተዳደር ኃላፊ ናቸው።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
128 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 179 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us