አሜሪካ ያለፈውን የኢትየጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ወቀሰች

Wednesday, 25 April 2018 12:26

 

·        በቀጣይ ተስፋ የሚታይ መሆኑንም አመለከተች

 

የአሜሪካ መንግስት የስቴት ዲፓርትመንት የሀገራት የሰብአዊ መብት አያያዝ ሪፖርት ከሰሞኑ ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚሁ ዙሪያ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ በድረገፁ ጋዜጣዊ መግለጫን ለቋል። ኢምባሲው በዚሁ መግለጫው ኢትዮጵያውያን በ2017 መሰረታዊ መብቶቻቸውን ለመጠቀም ሲያደርጉት በነበረው ጥረት ባለፈው ዓመት ከባድ ፈተና ገጥሟቸው ነበር ብሏል። ይኸው የኢምባሲው የፅሁፍ ጋዜጣዊ መግለጫ በቀጣይ በ2018 የሚወጣው የሀገሪቱ የሰበሰዓዊ መብት አያያዝ የተሻለ ይሆናል የሚል ተስፋ ያለው መሆኑን አመልክቷል።

 

መንግስት በፖለቲካው ዘርፍ በተለይም እስረኞችን በመፍታት የወሰዳቸው እርምጃዎችም በመልካም ጅምርነት የሚታዩ መሆኑን ጋዜጣዊ መግለጫው ጨምሮ አመልክቷል። በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በሀገሪቱ መሰረታዊ ለውጥን ለማምጣት የተገባውን ቃል ኢምባሲው የሚያበረታታ መሆኑን በዚሁ መግለጫ ተመልክቷል። ከዚህም በተጨማሪ የተገቡት ቃሎች ወደ መሬት እንዲወርዱ በሚደረገው ሂደትም መንግስት ሀገሪቱን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ይሄው ሪፖርት ያመለክታል። ሪፖርቱ የመንግስትን ያለፈውን ዓመት የሰብአዊ መብት አያያዝ በተመለከተ በዝርዝር በማየት ወቀሳ የሰነዘረ ሲሆን ቀጣዩ አካሄድ ግን ተስፋ የሚታይበት መሆኑን አመልክቷል።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
609 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 188 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us