ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሃዋሳ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ጋር ነገ ይወያያሉ

Wednesday, 25 April 2018 12:27

 

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሃዋሳ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ጋር ሊወያዩ ነው።

ውይይቱ የፊታችን ሃሙስ የሚደረግ ሲሆን፥ በነገው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃዋሳ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

በቆይታቸውም ከነዋሪዎቹ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ይሆናል። በተለይ በጌደዎ እና በጉጂዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕልባት ይሰጡታል ተብሎ ይጠቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሀገሪቷን የለውጥ እንቅስቃሴ በአንድ መስመር ውስጥ ለማስገባትና ቀጣይ የኢትዮጵያን የሰላምና የልማት ጉዞ ለማደላደል በጅግጅጋ፣ መቐለ፣ በጎንደር፣ በባሕር ዳር ከተሞች በመገኘት ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የሰላም ውይይቶች በሴራ ፖለቲካ አንዳንድ ቦታዎች ለመጥለፍ የተደረገው እንቅስቃሴ አብዛኛውን ሕዝብ ማስቆጣቱን ለማወቅ ተችሏል።¾

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
673 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 191 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us