የግብፅ ፓርላማ፤ አዲስ የፕሮፖጋንዳ አዋጅ በናይል ውሃ ላይ አጸደቀ

Wednesday, 25 April 2018 12:29

·        ከፍተኛ ውሃ የሚጠቀሙ ሰብሎችን መዝራት እስርና 3ሺ ዶላር ያስቀጣል፣

 

በለፈው እሁድ ዕለት የግብፅ ፓርላማ ከፍተኛ የውሃ ፍጆታ የሚጠቀሙት ሩዝ፣ ሙዝ እና ሌሎች ተመሳሳይ ሰብሎችን መኮትኮት እና መዝራት የሚከለክል አዋጅ አጽድቆ አውጥቷል። ለአዋጁ መውጣት በምክንያትነት ፓርላማው ያስቀመጠው፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግብፅ የምታገኘውን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ በከፍተኛ መጠን ይቀንሰዋል ከሚል ስጋት መሆኑ አሶሼትድ ፕሬስ ተዘግቧል።

የፀደቀው አዋጅ እንደሚለው፣ ከፍተኛ የውኃ ፍጆታ እንዳይጠቀሙ የወጣውን አዋጅ ተላልፈው የሚገኙ ግብፃዊያን እስርና የ3ሺ ዶላር የገንዘብ መቀጮ እንደሚጠብቃቸው ደንግጓል።

አዋጁ ሥራ ላይ የሚውለው በፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ፊርማ ሲጸድቅ ነው። በተያያዘም የኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ተከትሎ ግብፅ የቀይባሕር ውሃንን ጨውነት በመቀነስ ለመጠጥ ውሃ እና ለግብርና ሥራዎች ለማዋል እቅድ እንዳላት ፕሬዝደንት አልሲሲ ይፋ ማድረጋቸው ተዘግቧል።

የግብፅ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ የዓለም ዓቀፉን ሕብረተሰብ ያለውን አተያየት ለማንሸዋረር እና ውስጣዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ክስረታቸውን ውጫዊ ገፅ ለማስያዝ የተጠቀሙት ያረጀ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ቅጥያ አዋጅ መሆኑ የአደባባይ እውነት ነው።

የኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት መሆኑን በቃል ብቻ ሳይሆን፤ ከግብፅ፣ ከሱዳን እና ከኢትዮጵያ የተወጣጡ ከፍተኛ የቴክኒካል ቡድኖች አዋቅረው ያረጋገጡት፤ ጥሬ እውነት ነው። ይህ ሆኖ ሳለ የግብፅ ፖለቲከኞች የሕዳሴው ግድብ ወደ ግብፅና ሱዳን የሚፈሰውን የውሃ መጠን ለመቀነስ የተገነባ አድርገው ማቅረባቸው ከተፍጥሮ ባሕሪያቸው የማይላቀቁ መሆናቸውን ማረጋገጫ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።¾

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
807 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 185 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us