ንግድ ሚኒስቴር የዳቦ ስንዴ እጥረት ለመቅረፍ እየሠራሁ ነው አለ

Wednesday, 02 May 2018 12:33

መንግስት በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የዳቦ ስንዴ፣ ስኳር እና ፓልም የምግብ ዘይት ልዩ ድጎማ በማድረግ እያቀረበ ይገኛል። ይሁንና ሰሞኑን የዳቦ ስንዴ እጥረት በመከሰቱ በዱቄት ፋብሪካዎች እና በዳቦ ቤቶች የዳቦ ዱቄትና የዳቦ አቅርቦት ችግር ተሰተውሏል።

በጊዜያዊነት የተፈጠረውን የዳቦ ስንዴ እጥረት በመቅረፍ የዳቦ ስንዴ በሚፈለገው መጠን ለማቅረብ ከብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር እየተሰራ ነው ያሉት በንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ናቸው።

እንደ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ገለጻ ችግሩ የተፈጠረው በግዥ ሂደት መጓተት ምክንያት ነው። የስንዴ ግዥ የሚፈጸመው በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በኩል በፌዴራል ግዥ ኤጀንሲ አማካኝነት ሲሆን፤ ግዥውን ለመፈጸም የወጣው ጨረታ ከአንድም ሁለት ጊዜ ውድቅ የተደረገበት ሁኔታ ስለነበር ስንዴው በተፈለገበት ጊዜ ተገዝቶ ሳይቀርብ ቀርቷል።

በአሁኑ ወቅት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት ጋር በመተባበር ስንዴ እየቀረበ መሆኑን የገለጹት አቶ ወንድሙ ይህንን ጊዜያዊ ችግር ምክንያት በማድረግ የዳቦ ዱቄትና የዳቦ ዋጋ የሚጨምሩ እንዲሁም የዳቦ ግራም የሚቀንሱ አካላት ከድርጊታቸው መቆጠብ አለባቸው ያሉ ሲሆን፤ ይህንን ፈጽመው የተገኙ የንግድ አካላት ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

አቶ ወንድሙ አክለውም ሸማቹ ማኅበረሰብ አላስፈላጊ ዋጋ ሲጨምርና የዳቦ ግራም ሲቀንስ ነጋዴውን ለምን ብሎ በመጠየቅና ጥቆማ በመስጠት፣ ነጋዴውም የተቀመጠውን የግብይት ሥርዓት ጠብቆ በመስራት ጤናማ የሆነ ግብይት እንዲፈጠር የዜግነት ግዴታቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በ2010 በጀት ዓመት ያለፉት 9 ወራት ውስጥ 5 ሚሊዮን 5 ሺህ 219 ኩንታል ስንዴ የተሰራጨ ሲሆን፤ ይህም የእቅዱን 99 ነጥብ 9 በመቶ ነው ሲል የዘገበው በኢ.ፌ.ድ.ሪ ንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
589 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 180 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us