ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሒም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ሆነው ተሾሙ

Wednesday, 02 May 2018 12:35

·        የከተማ ፕላን ረቂቅ አዋጅ ውድቅ ሆነ

 

የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባዔ አቶ ያለው አባተ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ተከትሎ ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም የምክርቤቱ አፈጉባዔ ሆነው ተሾሙ።

ም/ቤቱ ትላንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የቀድሞ አፈጉባዔ የመልቀቂያ ጥያቄ በመቀበል ሹመቱን በሙሉ ደምጽ ተቀብሎታል።

ወ/ሮ ኬርያ የትግራይ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

አቶ ያለው አባተ ምክርቤቱን ከሁለት ዓመት ተኩል በላይ በአፈጉባዔነት አገልግለዋል።

በተያያዘ ዜና የፌዴሬሽን ም/ቤት ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበለትን የተከማ ፕላን ረቂቅ አዋጅ ሳይቀበለው ቀረ።

አዋጁ እያደገ ከመጣው የከተሞች መስፋፋት ጋር አብሮ የሚሄድ ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ ፕላን እንዲኖር እንደሚያደር ማብራሪያ የተሰጠበት ቢሆንም የም/ቤቱ አባላት አዋጁ እጅግ ዘግይቷል የሚል አቋም አንፀባርቀዋል።

ይህም ሆኖ አዋጁ በ30 ድጋፍ፣ በ60 ተቃውሞ፣ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
689 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1059 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us