300ሺ ዶላር የወጣበት የተቀናጀ ዲጂታል የህክምና አስተዳደር አገልግሎት አልተጠናቀቀም

Wednesday, 02 May 2018 12:36

-    ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግን ምርቃት ሊካሄድ ነው

 

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተዘርግቷል የተባለው የተቀናጀ ዲጂታል የህክምና አስተዳደር አገልግሎት የኢፌዲሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ይመረቃል።

የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዳሳወቀው፣ የተቀናጀ ዲጂታል የህክምና አስተዳደር አገልግሎት (Integrated Digital Health Management System) የታካሚዎቹን ሙሉ መረጃ በመያዝ ስርዓቱ በተዘረጋባቸው ሆስፒታሎች የታካሚው ሙሉ የህክምና መረጃ እንዲቀመጥ የሚያስችል ነው ብሏል። አያይዞም፣ የስርዓቱ ተግባራዊ መሆን የታካሚዎችን እንግልትን የሚቀንስ ሲሆን የሐኪሞችን ስራ ቀልጣፋ እንዲሆን በማገዝ ድካማቸውን ለመቀነስ ያግዛል።

ከዚህ በፊት ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ በ300ሺ ዶላር ያስጀመረው የተቀናጀ ዲጂታል የህክምና አስተዳደር አገልግሎት ፕሮጀክት የት እንደረሰ መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከአሜሪካ ቱሌ ዩኒቨርስቲ እና ሲዲሲ ጋር በመቀናጀት ጀምሮት የነበረው ፕሮጀክት የሶፍትዌር ፓኬጅ ግዢን ሳይጨምር ወደ 300ሺ ዶላር ወጪ እንደተደረገበት መረጃዎች ቢያሳዩም፣ ይህ ፕሮጀክት ወደ ሥራ ሳይገባ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የተቀናጀ ዲጂታል የህክምና አስተዳደር አገልግሎት ሊመረቅ ነው መባሉ ለባለድርሻ አካላት የተለየ ስሜት መፍጠሩን ለሰንደቅ ገልጸዋል፡፡

ጤና ጥበቃ ሚኒስትሩን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1069 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 763 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us