ከ1 ሺ በላይ ተማሪዎች የተካፈሉበት የኢትዮጵያ የሒሳብ ኦሎምፒያድ ውድድር፤ በኢንተሌክቹዋል ት/ቤት ተካሄደ

Wednesday, 02 May 2018 12:40

ባለፈው እሁድ ከ1ሺ በላይ ተማሪዎች የተካፈሉበት “የኢትዮጵያ የሒሳብ ኦሎምፒያድ” ውድድር በኢንተሌክቹዋልት/ቤት ተካሂዷል፡፡

የትምህርት ቤቱ ም/ርዕሰ መምህር አቶ ካሳሁን አስራደ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ “የኢትዮጵያ የሒሳብ ኦሎምፒያድ ውድድር በትምህርት ቤቶች መካከል የተጀመረው ከስምንት ዓመት በፊት ነው፡፡ ከ100 የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች በመጡ ተማሪዎች መካከል የተደረገ ውድድር ነው፡፡ ተሳታፊ የነበሩ ተማሪዎች ከሺ በላይ ናቸው፡፡” ብለዋል፡፡

ም/ርዕሰ መምህሩ ስለውድድሩ ዓላማ ሲያስረዱ፤ “ ዓላማው በአብዛኛው በሒሳብ ትምህርት ላይ ተማሪዎች ያላቸውን ፍርሃት ማስቀረትና ማብቃት ነው፡፡ የሒሳብ ትምህርት ሲባል “ይከበድኛል” “ከባድ ነው” የሚባሉ የተለመዱ አነጋገሮች አሉ፡፡ ከዚህ መነሻም የሒሳብ ትምህርት የመፍራት ዝንባሌዎች በአብዛኛው ተማሪ ዘንድ አለ፡፡ ውድድሩ እነዚህየተዛቡ አስተሳሰቦች ለማስተካከል እና ተማሪዎችንም በውድድር ለማብቃት ያለመ ነው፡፡ ከሚወዳደሩበት ትምህርት ቤት በላይ ተሻግረው በሀገር ደረጃ ጠቃሚ እና ተመራማሪዎች እንዲሆኑ እድል መፍጠር ነው፡፡ እንዲሁም እኛ በሒሳብ የጀመርነውን ውድድርና የማብቃት ሥራዎች ሌሎች ትምህርት ቤቶች በሌላ የትምህርት ዓይነት ተሳታፊ በመሆኑ ተማሪዎችን እንዲያበቁ መንገድ ለመጥረግም ጭምር ነው” ብለዋል፡፡

አያይዘውም፤ የትምህርት ቤቱ እቅድ በአዲስ አበባ የሚወሰን ሳይሆን በሀገር ደረጃ የሚዘጋጅ የሂሳብ ውድድር መፍጠር ነው፡፡ ከትምህርት ቤቶቹ ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት ከ100ሺ ብር በላይ በመመደብ ነው የሰራነው፡፡ በየዓመቱ የተሳታፊ ትምህርት ቤቶችና የተማሪዎች ቁጥር እያደገነው ያለው፡፡ አሁንም ብዙ ያልደረስንባቸው ትምህርት ቤቶች ስላሉ ከዚህ የበለጠ ሥራ ይጠብቀናል፡፡ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት ጥያቄም አቅርበናል ብለዋል፡፡

ውድድሩ የተሰጠው በትምህርት ቤቱ ሁለት ቅርንጫፎች ሲሆን አፍሪካ ሕብረት ጀርባ በሚገኘውና በዓለም ገና ትምህርት ቤት በሰበታ ወረዳ ውስጥ ነው፡፡ ለተማሪዎቹ ለውድድር የቀረበው የፈተና ወረቀት በአንድ ሰዓት ተኩል ጊዜ የሚጠናቀቅ ነበር፡፡ ውጤታቸውም በኤሌክትሮኒክ ማሽን ነው የታረመው፡፡

በጣም የሚገርመው የአዘጋጁ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በውድድሩ ተሳታፊ አይደረጉም፡፡ ምክንያቱም ደግሞ የበለጠ ውድድሩ ተአማኒነት እንዲኖረውና ተማሪዎች በፈተና ውጤታቸው ላይ በገለልተኛ መምህራን እንደሚዘጋጅና ፈተናውም እንደሚታረም እምነት እንዲኖራቸው ነው፡፡

ኢንተሌክቹዋል ትምህርት ቤት፤ ሁለት አጸደ ሕፃናት እና አንድ አንደኛ ደረጃ በአዲስ አበባ፣ በሰበታ ወረዳ ዓለም ገና ከኬጂ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤ፤ በመቀሌ ከኬጂ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በሐረር ከኬጂ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አለው፡፡

በውድድሩ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ ተማሪዎች ከ1ሺ እስከ 1ሺ 500 ብር ድረስ የገንዘብ ሽልማት፣ የእጅ ሰዓት እና ወክለው ለመጡበት ትምህርት ቤት ከለር ፕሪንተሮች ተሸልመዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በዝግጅቱ ላይ ያቀረቧቸው ባሕላዊና ዘመናዊ ዘፈኖች ና ጭፈራዎች ታዳሚውን በጣም ያዝናኑ ነበር፡፡ በተለይ በአንዳን ተማሪዎች ላይ የታየው አቅም ወደፊት ብዙ ደረጃ መድረስ እንደሚችሉ አመላካች ነው፡፡

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
1091 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 572 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us