ግብፅ፤ በኢትዮጵያና ሱዳን ላይ ክስ እያሰማች ነው

Wednesday, 09 May 2018 13:18

 

የህዳሴው ግድብ በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ ሊያደርስ በሚችለው ተፅዕኖና በግድቡ ውሃ አሞላል ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ግብፅና ሱዳን ሲያደርጉት የነበረው የአዲስ አበባው ድርድር መክሸፉን ተከትሎ ግብፅ በኢትዮጵያና ሱዳን ላይ ክስ እያሰማች ነው። የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ ከሰሞኑ የኡጋንዳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በካይሮ ያደረጉትን ቆይታ ተከትሎ ሁለቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ክሳቸውን ያሰሙት። እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ከሆነ የአዲስ አበባው ድርድር ሊሳካ ያልቻለው ግድቡ በታችኞቹ ሀገራት ላይ ሊያደርስው በሚችለው ተፅዕኖ ዙሪያ የቀረበውን ሪፖርት ሱዳን እና ኢትዮጵያ የማይቀበሉት መሆናቸውን በመግለፃቸው ነው። ሶስቱ ሀገራት ግድቡ ሊያደርስ በሚችለው ተፅዕኖ ዙሪያ ተከታታይ ውይይቶችን ቢያደርጉም ይህ ነው የሚባል መግባባት ላይ ያልደረሱ ሲሆን በቀጣይም በመጪው ግንቦት ወር 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሌላ ድርድር ለማድረግ ቀነ ቀጠሮ መያዛቸው ታውቋል።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በድርድሩ ዙሪያ የኢትዮጵያና የሱዳን አቋም ተመሳሳይነት የሚታይበት ነው። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ኢትዮጵያ ለልማት ያላትን ፍላጎት ግብፅ የምትረዳ መሆኑን ገልፀው ሆኖም ሂደቶች ቀደም ሲል በ2015 የሶስቱ ሀገራት መሪዎች በተስማሙት የመርሆ መግለጫ መሰረት ሊመራ ይገባል ብለዋል።

የግብፅ ክስና ቅሬታ አስመልክቶ በኢትዮጵያም ሆነ በሱዳን በኩል ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተባለ ነገር የለም። በቀጣይ በአዲስ አበባ የተያዘው የድርድር ቀነ ቀጠሮ እንደ ቀደሙት ድርድሮች የሚከሽፍ ከሆነ ቀጣይ ሊኖር የሚችለውን አካሄድ በተመለከተም የተባለ ነገር የለም። የሶስቱ ሀገራት ድርድር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአጭር ጊዜ ቀነ ቀጠሮ በተደጋጋሚ ያለ ምንም መግባባት እየተበተነ ነው። በግድቡ ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ድርድር ለተወሰነ ጊዜ መራዘም ግድ የሆነበት በኢትዮጵያ የተነሳውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ተከትሎ ኢትዮጵያ ድርድሩ እንዲራዘም በመጠየቋ ነበር።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
766 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1041 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us