የንግድ ሚኒስቴር የቀጥታ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

Wednesday, 09 May 2018 13:20

 

ንግድ ሚኒስቴር ለበርካታ ዓመታት የንግድ ስርዓቱን ለማዘመን እየሰራባቸው ከሚገኙ በርካታ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሆነውን የቀጥታ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት (online trade registration system)አሰጣጥን የሙከራ ትግበራውን አጠናቆ በፌዴራል ደረጃ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጅራታ ነመራ ገለፁ።

ዳይሬክቶሬቱ ከሚሰጣቸው 19 አገልግሎቶች መካከልም የንግድ ምዝገባ፣ አዲስ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት እና የንግድ ስም ስያሜ የማውጣት አገልግሎቶችን ተገልጋዮች በአካል መቅረብ ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ቦታ ሆነው አስፈላጊውን ቅፆች በመሙላት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እደሚችሉም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

የቀጥታ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አግልግሎት አሰጣጥ ስርዓት የማልማቱ ስራ በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኩል እንደተሰራ የገለፁት አቶ ጅራታ የአሰራር ስርዓቱ ተግባራዊነትም የንግዱ ማህበረሰብ ባለበት ቦታ ሆኖ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ቀልጣፋና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መልኩ እንዲያገኝ ከማስቻሉም በተጨማሪ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንም የሚቀርፍ እንደሆነ ገልፀዋል።

አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የአገልግሎት አሰጣጡ በፌዴራል ደረጃ ብቻ የተጀመረ ቢሆንም በቀጣይ በክፍለ ከተሞች፣ ክልልሎችና የከተማ አስተዳደር ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

የቀጥታ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጡ አዲስ እና በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድም ብዙ ያልታወቀ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለአገልግሎት የሚመጣው የንግድ ማህበረሰብ ቁጥር አናሳ መሆኑን የገለፁት አቶ ጅራታ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀጣይ አገልግሎት አሰጣቱን የማስተዋወቅ ስራዎች እንደሚሰሩ አብራርተዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም በፌዴራል ደረጃ የሚሰጡ አራቱንም አገልግሎቶች ለማግኘት የሚኒስትር መስሪያ ቤቱን ድረ-ገፅ ተጠቅመው አገልግሎቶቹን ማግኘት እንደሚችሉ ገልፀዋል።

በተያዘው የ2010 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስም 4ሺ 810 አዲስ የንግድ ምዝገባ፣ 11ሺ 317 አዲስ ንግድ ፍቃድ፣ 37ሺ 685 የንግድ ፍቃድ ዕድሳት እና በቁጥር 782 የንግድ ስም ማጣራትና የመመዝገብ አገልግሎቶች መስጠቱን የንግድ ሚኒስቴር ሕዝብ ግንኙነትና ኮምዩንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት ዘግቧል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1928 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1012 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us