ለአጼ ዮሐንስ አራተኛ

Wednesday, 09 May 2018 13:22

ለአጼ ዮሐንስ አራተኛ

በመተማ ዮሐንስ ሙዚየም፤ በተንቤን ደግሞ ሀውልትና ፋውንዴሽን ሊገነባላቸው ነው

በይርጋ አበበ

አጼ ዮሐንስ አራተኛ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ አገራቸውን ለ17 ዓመታት መርተው መተማ ዮሐንስ ላይ በሱዳን ጦር (መሀዲስት) አንገታቸውን ተቀልተው በተሰውበት ቦታ ሙዚየም ሊገነባላቸው ነው።

የንጉሰ ነገስቱ አራተኛ የልጅ ልጅ የሆኑት ራስ መንገሻ ስዩም ሙዚየሙን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን በገለጹበት ወቅት፤ የንጉሰ ነገስቱን ታሪክ የሚዘክርና ለትውልድ በሚያስተላልፍ መልኩ እንዲገነባ ከአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል።

በአጼ ኃይለሥላሤ ዘመነ መንግስት የትግራይ ክልል አስተዳዳሪ የነበሩት ራስ መንገሻ አክለውም ‹‹ንጉሰ ነገስቱ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው። በዚህ የተነሳም አኩሪ ታሪካቸው ለትውልድ በሚመጥን መልኩ ሊዘገብና መታሰቢያም ሊቆምላቸው ይገባል። ይህን በተመለከተ ከአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ጋር ባደረግነው ውይይት ሃሳባችንን ተቀብለው በከተማዋ የሚገነባውን ሙዚየም በገንዘብ እንደሚደግፉም አስታውቀውናል›› ብለዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አጼ ዮሐንስ አራተኛን የሚዘክር ሀውልት በትውልድ ቀያቸው ተንቤን ወረዳ እንደሚቆምላቸው ተገልጿል። ጉዳዩን የያዘው ኮሚቴ እንዳስታወቀው ንጉሰ ነገስቱን ለመዘከር በርካታ ስራዎች እንደሚሰሩ ገልጾ ‹‹ለጊዜው ሀውልታቸው ይቆማል፣ ፋውንዴሽንም ይመሰረታል። እንዲሁም ታሪካቸውን በዝርዝር የሚገልጽ መጽሀፍ ይታተማል›› ብሏል። ለፋውንዴሽኑ ግንባታም ከክልሉ መንግስት የ35 ሄክታር መሬት እንደተሰጠ ኮሚቴው ጨምሮ አስታውቋል።

ከአጼ ዮሀንስ አራተኛ በተጨማሪም በሚገነባው ፋውንዴሽን፣ ሙዚየም እና በሚቆመው ሀውልት ውስጥ የራስ አሉላ እንግዳ (አሉላ አባ ነጋ) ታሪክም የሚካተት መሆኑን አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተናግረዋል።

አጼ ዮሐንስ አራተኛ ከአጼ ቴዎድሮስ ሞት በኋላ ኢትዮጵያን ለሶስት ዓመታት ካስተዳደሩት አጼ ተክለጊዮርጊስ ላይ ስልጣኑን ተቀብለው አገራቸውን ለ17 ዓመታት የመሩ ኢትዮጵያዊ ንጉስ መሆናቸው ይታወቃል።

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
2066 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 890 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us