“በማንነት ላይ የሚደረግ ማፈናቀል ይቁም”

Wednesday, 23 May 2018 13:47

“በማንነት ላይ የሚደረግ ማፈናቀል ይቁም”

ሰማያዊ ፓርቲ

በይርጋ አበበ

ማንነትን መሰረት ያደረገ የዜጎች መፈናቀል እንደሚያሳስበውና ድርጊቱም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቆም ሰማያዊ ፓርቲ ገለጸ።

ፓርቲው ትናንት ማክሰኞ በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ “በዘርና በቋንቋ የኢትዮጵያን ህዝብ በመከፋፈል የአገዛዝ እድሜውን በማራዘም የቀጠለው አምባገነኑን የአህአዴግ አገዛዝ ለዘመናት ተዋዶና ተፈቃቅዶ የኖረውን የአገራችንን ህዝብ ማህበራዊ እሴቶችና ግንኙነቶችን በፈጠራ ታሪኮች፣ በተንኮልና በጥላቻ በመበረዝ የአገር አንድነት በማናጋት አገዛዙ የዜጎችን ሰላማዊ ኑሮ ክፉኛ እያናወጠው ይገኛል” ብሏል።

ፓርቲው በመግለጫው አክሎም “የኢህአዴግ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያከትም የተጀመረው ህዝባዊ ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል” ያለ ሲሆን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በዜጎች ላይ ኢ-ሰብአዊ ጥቃት እየተፈጸመ ይገኛል፤ ይህም በአገዛዙ የታች ሹሞች እና ተልዕኮ ፈጻሚዎች አማካኝነት እየተከወነ መሆኑን አስታውቋል።

ኢህአዴግ በ1983 ዓ.ም ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በመላው የአገሪቱ ክፍሎች የደረሱ የዜጎችን ሞት፣ መፈናቀል፣ መታሰርና መሰደድ የዘረዘረው ሰማያዊ ፓርቲ፤ ይህን ድርጊትም ፓርቲው በጽኑ ሲያወግዘው መቆየቱን ገልጿል። ድርጊቱንም “የአገዛዙን የጥላቻ ዘር በግልጽ ያሳየ መጥፎ አጋጣሚ ጭምር ነው” ያለው ሰማያዊ ፓርቲ፤ ‹‹የአገዛዙ ግፍ እና በደሎች ከትላንት ዛሬ እየከፋ መጥቶ ዜጎች ለዘመናት ሲኖሩ ከነበሩበት አካባቢ እንዲፈናቀሉ እየተደረገ ይገኛል። ዛሬም በአማራ ማህበረሰብ ተወላጆች ላይ በገዥው ፓርቲ የሥራ ኃላፊዎች ትዕዛዝ ሰጪነት እየተፈጸመባቸው የሚገኘውን እጅግ አስከፊ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሰማያዊ ፓርቲ በጽኑ ያወግዛል›› ብሏል።

ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው መጨረሻም በቅርቡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ዝግህ በሚባል አካባቢ ከብት ጥበቃ ላይ በነበረ የ14 ዓመት ታዳጊ የደረሰውን የ“መሰለብ” እና ዐይኑን የማጥፋት ድርጊት በጽኑ ኮንኖ ድርጊቱን የፈጸሙትም ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
3768 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 138 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us