የቀድሞ የኦነግ አመራሮች ለድርድር ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ

Wednesday, 23 May 2018 13:48

 

ጠ/ሚ አብይ አሕመድ ለሠላማዊ ድርድር በጋበዙት መሠረት በአንድ ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ተብሎ የሚጠራ ፓርቲ መሪዎች የሆኑ አምስት ሰዎች ዛሬ ረቡዕ ማለዳ ለተጨማሪ ድርድር አዲስአበባ እንደሚገቡ ተሰማ።

በዛሬው ዕለት ይገባሉ ከተባሉት መካከል፡- አቶ ሌንጮ ለታ (የኦነግ ዋና ፀሀፊ የነበሩ)፣ ዶ/ር ዲማ ነጎዎ (የኦነግ ሊቀመንበር የነበሩ)፣ ዶ/ር በያን አሶባ (የኦነግ ቃል አቀባይ የነበሩ)፣ ዶ/ር ሀሰን ሁሴን (የኦነግ አመራር አባል የነበሩ)፣ አቶ ሌንጮ ባቲ  (የኦነግ ቃል አቀባይ የነበሩ) እንደሚገኙበት ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

   የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባርን ተከትለዉ፣ በጄኔራል ኃይሉ ጎንፋ፣ በጀኔራል ከማል ገልቹ፣ በአቶ ገላሳ ዲልቦ የሚመሩ የኦሮሞ ድርጅቶችም በቅርቡ ወደሀገር ገብተው ተመሳሳይ ድርድር በማድረግ ሠላማዊ ትግሉን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳምንታት በፊት ከኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር አመራሮች ጋር በዋሽንግተን ዲሲ የመጀመሪያውን ድርድር ያካሄደ ሲሆን የተደረገው ድርድር የተሳካና ሃገራዊ መግባባት የሰፈነበት እንደነበር የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ መጥቀሱ የሚታወስ ነው።¾

ይምረጡ
(4 ሰዎች መርጠዋል)
3806 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 49 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us