የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የፋይናንስ ሕግና ሥርዓትን መጣስ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል

Wednesday, 06 June 2018 13:21

 

የመንግሥትን የግዥ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ሳይከተሉ ግዥዎችን በመፈጸም ረገድ ሰባት ዩኒቨርሲቲዎች በዋንኛነት እንደሚገኙበት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በቅርቡ ይፋ ባደረገው የ2009 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርቱ አስታወቀ።

በሪፖርቱ መሠረት የዕቃና የአግልግሎት ግዥ በመንግሥት ደንብና መመሪያ መሠረት የተፈጸመ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ በ97 መ/ቤቶችና 6 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ያለጨረታ ቀጥታ ግዥ፣ መስፈርቱ ሳይሟላ በውስን ጨረታ ግዥ በመፈጸም፣ የዋጋ ማወዳደሪያ ሳይቀርብ የተፈጸመ ግዥና ሌሎች የግዥ ሂደት ያልተከተሉ በድምሩ ብር 487 ሚሊየን 958 ሺ 696 ከ75 ሳንቲም ተገኝቷል።

ከግዥ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ውጭ ግዥ ከፈጸሙ መ/ቤቶች መካከል የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ 61 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር፣ የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ 61 ሚሊየን፣ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ 43 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር፣ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ 39 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ 29 ሚሊየን ብር፣ የመቱ ዩኒቨርሲቲ 21 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር፣ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ 21 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር፣ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 12 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በማስመዝገብ ዋናዋናዎቹ ናቸው ሲል የፌዴራል ዋና ኦዲተር ተናግሯል።

ዋና ኦዲተሩ አያይዞም በሌሎች አምስት የመንግስት መ/ቤቶች የተገዙት ዕቃዎች በናሙናው መሠረት ገቢ ለመሆናቸው ሳይጣራና የተጠየቀው አገልግሎት ስለመሰጠቱ በባለሙያ ወይም በቴክኒክ ኮምቴ ሳይረጋገጥ ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ከፍያ ተፈጽሞ ተገኝቷል ብሏል።

የግዥ መመሪያን ሳይከተሉ ግዥን መፈጸም የህግ ጥሰት ነው ያለው ዋና ኦዲተር፣ ሕግ መጣሱ ደግሞ መንግሥት ተወዳዳሪ ዋጋ እንዳያገኝ ለምዝበራና ለጥራት መጓደል፣ ለግብር ስወራ ጭምር የሚያጋልጥ ነው ብሏል።

አያይዞም የመንግስት ግዥ ደንብና መመሪያን አክብረው በማይሰሩ መ/ቤቶች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲል አሳስቧል።

በተለይ የተማረ የሰው ኃይል የሚያፈሩና አርአያ ሆነው መገኘት ለባቸው፣ እንዲሁም አንጻራዊ በሆነ መልኩ በተማረ የሰው ኃይል ተደራጁት ከፍተና የትምህርት ተቋማት የግዥ መመሪያና ደንብን የጣሰ አሠራር መፈጸማቸው፣ አንዳንዶቹም ጥፋታቸው ተደጋጋሚ መሆኑ በአሳፋሪነቱ መነጋገሪያ ሆኖ የከረመ መሆኑን ተከትሎ መንግሥት በአጥፊ አመራሮች ላይ በሕግ እንዲጠየቁ ሕዝባዊ ግፊት እያየለበት መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
2378 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1041 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us