ሰብአዊ መብታችን በአ/አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተጥሷል ያሉ ካህናትና ሠራተኞች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጣልቃ ገብነት ጠየቁ

Wednesday, 06 June 2018 13:26

 

·         ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነላቸውን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ተፈጻሚ አላደረጉም

·         የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም፣ ወደ ሥራቸው አልተመለሱም

 

ውዝፍ ደመወዛችን ተከፍሎን ወደ ሥራችን እንድንመለስ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንም ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ውሳኔውን ተፈጻሚ ባለማድረጋቸው ሰብአዊ መብታችን እየተጣሰ ነው፤ ያሉ ስድስት የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናትና ሠራተኞች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጣልቃ ገብነት ጠየቁ፡፡

በተለያዩ አድባራት የሚሠሩ ሦስት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ሦስት ካህናትና ሠራተኞች፣ ባለፈው ሰኞ ግንቦት 23 ቀን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛው ወሳኝና ሕግ አውጭ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ውዝፍ ደመወዛቸው ተከፍሏቸው ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ያሳለፈው ውሳኔ በቅዱስ ፓትርያርኩ በኩል እንዲፈጸምላቸው ይደረግ ዘንድ ጠይቀዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔውን የሰጠው፣ ከአንድ ወር በፊት፣ ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ እንደኾነ የገለጹት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፤ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መ/ር ጎይትኦም ያይኑ ግን“ውሳኔውን ወደ ጎን በመተውና ሥልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም ተፈጻሚ ባለማድረጋቸው” ከነቤተቦቻቸው ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው እንዳለ ተናግረዋል፡፡

የጉዳዩ መነሻ፣ ሀገረ ስብከቱ በአቤቱታ አቅራቢዎቹ ላይ ያሳለፈውን ከሥራና ደመወዝ የማገድ፣ የማሰናበትና የማዛወር ውሳኔ በመቃወም በመንፈሳዊ ፍ/ቤት የቀረበ አቤቱታ መኾኑ ተገልጿል፡፡ መንፈሳዊ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ፣ አቤቱታ አቅራቢዎቹ ውዝፍ ደመወዛቸው ተከፍሏቸው ወደየሥራቸው እንዲመለሱ፣ በአስተዳዳሪነት ሓላፊነት ያሉትንም ለፓትርያርኩ አስቀርቦ እንዲያስመድብ ወስኖላቸዋል፡፡ሀገረ ስብከቱ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ቢጠይቅም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሀገረ ስብከቱን መንፈሳዊ ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቶታል፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት፣ ከፍተኛው መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ሕግ አውጭና ወሳኝ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ እንደመኾኑ፣ ሀገረ ስብከቱ የይግባኝ አቤቱታውን የቅዱስ ሲኖዶሱ አስፈጻሚ አካል ለኾነው ቋሚ ሲኖዶስ አቅርቧል፡፡

እነመጋቤ ሃይማኖት መንግሥቱ ድረስ በሚል መዝገብ፣ በሀገረ ስብከቱ መንፈሳዊ ፍ/ቤት የቀረበውን የስድስት ካህናትና ሠራተኞች ክሥ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱን የይግባኝ አቤቱታ፣ ባለፈው ጥር ወር በሠየመው ኮሚቴ አማካይነት ሲያጠና የቆየው ቋሚ ሲኖዶስ፣ ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ፣ ፓትርያርኩ ያቀረቡትን የኮሚቴውን የሕግ አስተያየትና የውሳኔ ሐሳብ በመመርመር ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚህም መሠረት፦ መጋቤ ሃይማኖት መንግሥቱ ድረስ፣ መልአከ ገነት አባ ሀብተ ማርያም ቦጋለ እና መልአከ መዊዕ አባ ኃይለ ሥላሴ ገብረ ጊዮርጊስ የተባሉት ሦስት የአድባራት አለቆች፣ ውዝፍ ደመወዛቸው ተከፍሎ ወደ አስተዳዳሪነት ሥራቸው እንዲመለሱ ተወስኖላቸዋል፡፡

በተመሳሳይ ኹኔታ፥ ከሥራና ከደመወዝ የታገዱበት ምክንያት በፍ/ቤት ታይቶ በነጻ የተሰናበቱት ዲያቆን ዘውገ ገብረ ሥላሴ እና አላግባብ እንዲሰናበቱ የተደረጉት መሪጌታ ዳንኤል አድጎ እንዲሁም ወደ ሌላ ደብር መዛወራቸውን የተቃወሙት መ/ር መሣፍንት ተሾመ በዲቁና ሲያገለግሉበት ወደነበረው ካቴድራል ውዝፍ ደመወዛቸው፣ የበዓል ቦነሳቸውና ወጪና ኪሳራቸው ተከፍሏቸው እንዲመለሱ የሀገረ ስብከቱ መንፈሳዊ ፍ/ቤት በወሰነው መሠረት እንዲፈጸምላቸው ቋሚ ሲኖዶሱ ወስኖላቸዋል፡፡

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የውሳኔውን ቃለ ጉባኤ በማያያዝ፣ ሀገረ ስብከቱ እንዲስፈጽም ሚያዝያ 18 ቀን በጻፈው ደብዳቤ ትእዛዝ መስጠቱንና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንም ውሳኔው ተግባራዊ እንዲኾን ማስጠንቀቁን የጠቆሙት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፣ ሥራ አስኪያጁ ግን፣“በማናለብኝነት ተፈጻሚ አለማድረጋቸውን” ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ አስታውቀዋል፡፡ “በእኛም ኾነ በሥራችን በምናስተዳድራቸው ቤተሰዎቻችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱብን ነው፤” በማለት ምሬታቸው የገለጹ ሲኾን፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈው ውሳኔ በፓትርያርኩ እንዲፈጸም ጽ/ቤቱ ጣልቃ ገብቶ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

አቤቱታው በፖስታ ቤት በኩል የደረሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት፣ ከትላንት በስቲያ ጠርቶ እንዳነጋገራቸውና ማብራሪያም እንደጠየቃቸው የጠቀሱት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፣ ለመጪው ዐርብ እንደቀጠራቸውና ስለጉዳዩ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ ሊመክርበት እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ “የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ በማስፈጸም አልያም በሰብአዊ መብት ኮሚሽኑ ማስጠንቀቂያ መሠረት ሀገረ ስብከቱን በሕግ ተጠያቂ በማድረግ ለከፋ እንግልት የተጋለጠንበት ችግር እልባት ያገኛል ብለን እንጠብቃለን፤” በማለት ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡

ቋሚ ሲኖዶሱ የይግባኝ አቤቱታውን እየመረመረ በነበረበት ወቅት ስለጉዳዩ በአዲስ አድማስ የተጠየቁት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መ/ር ጎይትኦም ያይኑ በሰጡት ምላሽ፣ ደረጃውንጠብቀንነውየምንሔደው፤መንፈሳዊ /ቤቱወስኖልንተግባራዊአልኾነልንምየሚሉሰዎች፣ቋሚሲኖዶሱይመለሱብሎከወሰነ የማይመለሱበትምክንያትየለም፤” ብለው እንደነበር፤ በመታየት ላይ ያሉ ጉዳዮች ውጤት ሳይታወቅ ምደባዎች ተደርበው ስለሚሰጡበት ኹኔታም፣ “ይኼሊኾንየማይችልነው፡፡እኛሕጋዊመስመሩንተከትለን፣የስንብትደብዳቤጽፈንከለቀቁበኋላነውሠራተኛየምንመድበው፤” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ተወስቷል፡፡

ሥራ አስኪያጁ ይህን ይበሉ እንጅ፣ ከአቤቱታ አቅራቢዎቹ መካከል፣ መጋቤ ሃይማኖት መንግሥቱ ድረስ ከውሳኔው በኋላ ቀደም ሲል በነበሩበትና ጥፋታቸው በማስረጃ ሳይረጋገጥ ከተነሡነበት ደብር ውጭ በእልቅና ቢመደቡም፣ ደብሩ ሙሉ ደመወዛቸውን ለመክፈል እንደማይችል አስታውቋቸዋል፤ በተመሳሳይ ኹኔታ መልአከ ገነት አባ ኃይለ ማርያም ቦጋለ፣ እገዳቸው ታይቶ ቢነሣላቸውም፣ በቦታቸው ላይ ሌላ አስተዳዳሪ በመመደቡ እየተጉላሉ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመቀበል ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
2580 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 817 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us