መንግሥት በየመን የባህርዳርቻ ላለቁት ወገኖቻችን ሐዘኑን ገለጸ

Wednesday, 13 June 2018 12:56

የኢ.ፌ.ድ.ሪ. መንግስት በየመን የባህር ጠረፍ የደረሰን የጀልባ አደጋ አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በዜጎቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ።

 

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በላከው መግለጫ እንዳስረዳው አደጋ መድረሱ እንደተሰማ ወደስፍራው ሰዎችን በማሰማራት፣ በአካባቢው የሚገኙ ኤምባሲዎቻችንን በማንቀሳቀስ እና የመን እና አዲስ አበባ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ጋር በመሆን አደጋውን በቅርበት ተከታትሏል። በተደረገው ክትትል 46 ያህል ዜጎቻችን በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ለመረዳት ተችሏል።

 

መንግሥት ከተባበሩት መንግሥታት የፍልሰት ድርጅት እንዲሁም ከአደጋው የተረፉ ወገኖች ጋር ባደረገው ክትትል ለመገንዘብ እንደተቻለው 100 ያህል ኢትዮጵያውያንን የጫነች ጀልባ ከቦሳሶ ሶማሊያ ተነስታ ስትጓዝ ካደረች በኋላ ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ.ም የመን የባህር ጠረፍ ላይ ስትደርስ በደረሰባት አደጋ 46 ሰዎች ሲሰጥሙ 15 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።

 

ቀሪዎቹ ከአደጋው የተረፉ 39 ወገኖቻችን በአካባቢው የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ጋር በመተባበር የመን ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ የህክምና ድጋፍ እንዲሰጣቸው እያደረጉ ነው። መንግሥት በዜጎቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል ብሏል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1043 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 103 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us