ከኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆችን ያፈናቀሉ ባለስልጣናት ተሰናበቱ

Wednesday, 13 June 2018 12:58

በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ ለማድረግ ሲሞክር አንድ የተደራጀ ቡድን በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

 

በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን አፈናቅላችኋል፣ ወይም ለማፈናቀል ሞክራችኋል፣ ጥላቻን ዘርታችኋል፣ ወይም ህዝብ ለህዝብ እንዲጣላ ምክንያት ሆናችኋል የተባሉ የዞን፣ የወረዳ፣ የቀበሌና የልዩ ልዩ ቀበሌዎች አመራሮችን አሰናብተዋል፣ የአንዳንዶቹም በህግ እንዲታይ አድርገዋል ብሏል የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ድርጅት በዘገባው።

 

“..የአማራ ህዝቦች ወንድሞቻችን ናቸው፣ ያለ እነሱ እነሱም ያለኛ.. ወይም አንዳችን ያለ አንዳችን መኖር አንችልም..በቅርቡ የመጣውን ለውጥ እንኳን ተመልከቱ፣ የሁሉቱ ክልል ህዝቦች ትግል ነው..አሁን የምታዩት ለውጥ ያመጣው… የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች በአማራ ክልል ያለምንም ችግር እየኖሩ ነው፣ ስለሆነም ወንድሞቻችን በኦሮሚያ ክልል ያለምንም ስጋት ሰርተው እራሳቸውን መለወጥ፣ ሀብት ማከማቸት ይችላሉ፣ አንዳንዶች በኦሮሚያና በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ አለመተማመንን ለመፍጠር እየተሯሯጡ እንደሆነ በዚህ ሳምንት የታየ ድርጊት መሆኑን አረጋግጫለሁ፣ ስለዚህ የሁለቱ ክልል ህዝቦች ይህንን ሴራ መመከት ያስፈልጋል..” ..ሲሉ ፕረዚዳንት ለማ መገርሳ ተናግረዋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1116 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 102 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us