አዲሱ የአሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እውቅና አገኘ

Wednesday, 13 June 2018 12:59

በይርጋ አበበ

አምስት የፌዴሬሽን አባላትን ይዞ የተመሰረተውና ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ.ም የመሥራች ጉባኤውን ያካሄደው አዲሱ የአሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የእውቅና ደብዳቤ ሰጥቶታል።

የሚኒስትሩ መስሪያ ቤቱ በደብዳቤ እንደገለፀው “በአዲስ የተደራጀው ኮንፌዴሬሽን ግንቦት 16/2010 ዓ.ም ባካሔደው መስራች ጉባኤ መተዳደሪያ ደንቡን በማጽደቅና አመራሩን በመምረጥ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲመዘገብ እና የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጣችሁ ኢአኮአም /0436/10 በ16/09/2010 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ መጠየቁ ይታወሳል።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀጽ 34 እና በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 377/96 መሠረት ኮንፌዴሬሽኑ ህጋዊ ሆኖ ተመዝግቧል” በማለት በኢትዮጵያ እውቅና የተሰጠው የአሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን መሆኑን አስታውቋል።

የአሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን መሥራች ጉባኤ ግንቦት 16 ቀን በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ 11 አባላት ያሉት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የመረጠ ሲሆን እነዚህን ሥራ አስፈፃሚዎችም ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀብሎ እውቅና ሰጥቷቸዋል።

ለአራት ዓመታት በሚቆየው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች የሥራ ዘመን ኮንፌዴሬሽኑን ኢንጂነር ጌታሁን ሁሴን በሊቀመንበርነት የሚመሩት ሲሆን አቶ ፍትህ ወልደሰንበት ደግሞ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸው።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
1118 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 82 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us