``የኢህአዴግን ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የአልጀርሱን ሥምምነትም አረና አይቀበለውም”

Wednesday, 13 June 2018 13:01

``የኢህአዴግን ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የአልጀርሱን ሥምምነትም አረና አይቀበለውም”

አቶ አብርሃ ደስታ

በይርጋ አበበ

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከ18 ዓመት በፊት በአልጀርስ የተፈረመውን የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ኮሚሽንና ስምምነት ያለቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኑን በመቃወም አረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉአላዊነት (አረና) የፊታችን ቅዳሜ በመቀሌ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ።

የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ትላንት ማምሻውን በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢህአዴግ ያስተላለፈውን ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የአልጀርሱን ስምምነትም አንቀበለውም” ሲሉ ተናግረዋል። የአረናው ሊቀመንበር አያይዘውም በዚህ የተነሳም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 9 2010 ዓ.ም በመቀሌ ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት መገደዳቸውን ተናግረዋል።

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በኢሮብ፣ ባድመ፣ ዛላንበሳ እና ሌሎች የትግራይ ክልል ከተሞችም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች መካሄዳቸውን የጠቆሙት አቶ አብርሃ ሰልፎቹ የሚካሄዱት በተለይ በድንበር አካባቢ ባሉ ከተሞች የህወሓት አመራሮችም የሚያስተባብሩት እንደሆነ ተናግረዋል።

ሰልፎቹን እንዲካሄዱ ፓርቲያችሁ ምን አስተዋፅኦ አድርጓል ተብለው የተጠየቁት አቶ አብርሃ “እኛ ውሳኔውን ህዝቡ ለተቃውሞ እንዲወጣ ከማወጅ በዘለለ እስካሁን የመራነው ሰልፍ የለም። የቅዳሜውን ግን እኛ የጠራነው ሲሆን ለሚመለከተው አካልም አሳውቀናል” ብለዋል።

“በህወሓት አገዛዝ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ተከልክሎ ቆይቷል” የሚሉት አቶ አብርሃ ደስታ፤ “በቅዳሜው ሰልፍ ግን በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ እንደሚታደም እንጠብቃለን፣ ምክንያቱም ይህ አገራዊ ጉዳይ ነውና” ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ አብርሃ በመጨረሻም “ኢህአዴግ አሁን ያለበት ሁኔታ አገር ለመምራት የሚያስችለው ብቃት ላይ አይደለም። ሁሉም ነገር ከቁጥጥሩ ውጭ ሆኖበታል። ስለዚህ ሁሉን አሳታፊ የሆነ የአንድነት መንግሥት እንዲመሰረት እንጠይቃለን” በማለት የፓርቲያቸው አረናም እና የመድረክ አቋም አንፀባርቀዋል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
1214 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1019 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us