መንግሥት የዕዳ ጫና ውስጥ መዘፈቁን በይፋ አመነ

Wednesday, 13 June 2018 13:07

-    አጠቃላይ ዕዳው 26 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ተሻግሯል

 

የኢትዮጵያ የብድር ዕዳ ጫና ከፍተኛ ወደሚባል ደረጃ መሄዱና ሀገር ውስጥ ለሚገቡ ምርቶች የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመከሰቱ የመንግስትን የልማት ድርጅቶችን በአክስዮን ለመሸጥ ውሳኔ ላይ መደረሱን የብሄራዊ የፕላን ኮሚሽን ይፋ አደረገ።

የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) በበኩሉ የኢትዮጵያ የብድር ጫና ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ የብድር ጫና እንደገባና የብድር ምጣኔዋም የአጠቃላይ አመታዊ ምርቷን 59 በመቶ መያዙን አስታውቀዋል።

የብሄራዊ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ይናገር ደሴ እንዳሉት፣ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በወጭ ንግድ መዳከምና በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ አደጋ ውስጥ መግባቱን አምነዋል። አያይዘውም፣ ባለፉት ጥቂት አመታት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች የሚገኘው ገቢ በአማካይ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ላይ ሲሆን፣ ከውጭ ምርቶችን ለማስገባት የሚወጣው የውጭ ምንዛሪ ደግሞ 16 እና 17 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ብለዋል።

ዶክተር ይናገር ደሴ አያይዘውም፤ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች ሙሉ ለሙሉ የሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ከተላኩት ምርቶች የማይገኝ መሆኑም ኢኮኖሚውን ጤነኛ አላደረገውም፤ ይህ ደግሞ ሀገሪቱን የእዳ ጫና ውስጥ እንደጨመራት አስረድተዋል።

የብሄራዊ የፕላን ኮሚሽነሩ ዶክተር ይናገር ስጋታቸውን ሲያስቀምጡ፤ “ሀገሪቱ አሁን ላይ ወደ ከፍተኛ የብድር ጫና ውስጥ እየገባች ነው። በዚህ ምክንያትና ኢኮኖሚውን ማንቀሳቀሻ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ስለሚያስፈልግም መንግስት ውሳኔ አሳልፏል። ለአሁኑ የውሳኔ አስፈላጊነት ጥቂት ቁጥሮችን በማሳያነት አስረድተዋል፤ የሀገሪቱ አጠቃላይ እዳ 26 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ተሻግሯል። ይህ ሁኔታ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ምርት ጋር ሲታይ አንድም የውጭ ባለሀብቶችን እንዳይመጡ ያደርጋል። በሌላ በኩል የባለሀብቶች መተማመንን ያጠፋል” ብለዋል።

ዶክተሩ አክለውምየውጭ ምንዛሪ እጥረትና በሌላ በኩል ሀገሪቱ ለቀጣይ ሁለት አመታት ብድር ለመክፈል ስድስት ቢሊየን እንዲሁም፥ የመንግስት ፕሮጀክቶችን ለሁለት አመታት ለማከናወን ደግሞ ሰባት ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ያስፈልጋታል። ይህ በመንግስት በኩል የሚፈለግ ሲሆን እንደ ነዳጅና ሌሎች የፍጆታ ሸቀጦችን ማስገቢያና የሁሉም ዘርፍ ሲታይ ደግሞ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት እጅጉን ከፍ ያደርገዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

`ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቱ የብድር ደረጃዋ ከከፍተኛዎቹ ይመደባል የሚለውን ሳይቀበል ቆይቷል። እንደ ስኳር ላሉ ፕሮጀክቶች የተወሰደው ብድር ደግሞ ወደ ምርት ሳይገባ እዳ መክፈያው ጊዜ ደርሷል፤ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችቷን በሚፈለገው ደረጃ ለማስቀጠል ጥረት አድርጋ ቢሳካላትም አሁን ላይ ግን መንገዳገድ ውስጥ በመገባቱ እርምጃው አስፈልጓል። እነዚህ ምክንያቶች ተደማምረው የፈጠሩት ችግር ለመንግስት ውሳኔ ምክንያት መሆኑን” ዶክተር ይናገር ገልጸዋል።

ሀገሪቱ እዚህ እጥረት ውስጥ የገባችው በግብርና እና ኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ የታሰበው ባለመሳካቱ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሩ፥ እነዚህን ለማስተካከል የረጅም ጊዜ አቅጣጫ ተቀምጠዋል። የአሁኑ እርምጃም የአጭር ጊዜ ነው። ኢኮኖሚው በቀጣይ አመታት በወጭ ንግድ አፈጻጸም ታግዞ እንዲቀጥል በተለይም ግብርናውን እና አምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍና ለውጥ እንዲመጣ አቅጣጫ ተቀምጧል። ላለፉት አመታት በጥሩ ሁኔታ የመጣውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ውድቀት ውስጥ እንዳይገባም የአሁኑ ፕራይቬታይዜሽን እንደ መፍትሄ መቀመጡን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

ሳምንት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለፈው ሣምንት ባደረገው ስብሰባ በሀገሪቱ ባልተለመደ ሁኔታ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጦችን የሚያመጡ ውሳኔዎች አስተላልፏል። ይኸውም፣ በመንግስት እጅ ያሉ ሆቴሎች፣ የባቡር፣ የስኳር ልማት፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ እና የተለያዩ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች፥ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በአክስዮን ሽያጭ ወደ ግል ዘርፍ እንዲተላለፉ ውሳኔ አሳልፏል።

እንዲሁም፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች እና የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት ትልቁን ድርሻ መንግስት ይዞ ቀሪው አክስዮን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች እንዲተላለፍም መወሰኑ ይታወሳል።¾

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
1241 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 697 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us