የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የታሰሩ አባሎቹ በመፈታታቸው መደሰቱን ገለጸ

Wednesday, 20 June 2018 12:46

* የሕዝቡ ጥያቄም እንዲመለስ አሳስቧል

 

የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ወ.ህ.ዴ.ፓ) የወለኔን የማንነት ጥያቄ በማቅረባቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ አባሎቹ መንግሥት በገባው ቃል መሠረት በይቅርታ ሰሞኑን መለቀቃቸው እንዳስደሰተው ገለጸ። ፓርቲው አያይዞም አባሎቹ ሕገመንግሥታዊ መብታቸውን በመጠየቃቸው ለእስር የተዳረጉበት፣ የተጎዱበት ጥያቄ አፋጣኝ መልስ እንዲሠጠው ጠይቋል።

የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አብዲ ተማም ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደተናገሩት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በ2004 ዓ.ም የወለኔ የማንነት ጥያቄ መነሻነት ግጭት ተቀስቅሶ የተወሰኑ የፓርቲው ከፍተኛ አመራርና አርሶአደር አባሎቻቸው የመንግስት መዋቅር አፍርሰዋል፣ ሕዝቡን አሳምጸዋል፣ ያልተፈቀደ ስብሰባ አድርገዋልና የመሳሰሉ ምክንያቶችን በመጥቀስ ከ60 በላይ የፓርቲው አባሎች ታስረው እንደነበር አስታውሰዋል። ሆኖም የፓርቲው ከፍተኛ አመራር በፍርድ ቤት በነበረው ክርክር በነጻ እንዲሰናበቱ መወሰኑን ተከትሎ የታሳሪዎች ቁጥር ቀንሷል ብለዋል።

የተቀሩ ታሳሪዎች ከ3 እስከ 15 ዓመት እስር ተፈርዶባቸው የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ከወጡት ሌላ የ65 ዓመት አዛውንት ጨምሮ 11 ያህል የፓርቲው አባላት እስከያዝነው ወር የመጀመሪያ ሳምንት ድረስ በእስር ላይ ቆይተው ኢህአዴግ በወሰነው መሠረት በይቅርታ ሰኔ 9 ቀን 2010 ዓ.ም ታሳሪዎቹ መለቀቃቸውን አረጋግጧል። ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግና መንግሥት እስረኞችን በመልቀቅ ረገድ የወሰዱት እርምጃ በገንቢነቱ እንደሚመለከተው የፓርቲው ሊቀመንበር ጠቁመው ነገርግን የወለኔ ሕዝብ በሕገመንግሥቱ መሠረት ያቀረበው የራስን በራስ የማስተዳደርና በራስ ቋንቋ የመማርና የመዳኘት ጥያቄ በአፋጣኝ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት አሳስበዋል። ሊቀመንበሩ እንዳሉት ስለሁኔታው የክልሉ የብሄረሰቦች ምክርቤት ተገቢውን ጥናትና መረጃ መሰብሰቡን አስታውሰው ነገርግን ውሳኔው ከዛሬ ነገ ይሰጣል እየተባለ አለአግባብ መጓተቱን በማስታወስ ሒደቱ እንዲፋጠንና የህዝቡ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ጠይቀዋል።

የወለኔ ሕዝብ ባለፉት ዓመታት መብትና ጥቅሞቹን ለማስከበር እልህ አስጨራሽ ሠላማዊ ትግል ማድረጉን በማስታወስ በቀጣይ ከክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ጋር ለመወያየት ዕድል እንዲመቻችለት ፓርቲው ጥረት እያደረገ መሆኑን ሊቀመንበሩ ጠቁመዋል።

ሰሞኑን ከወልቂጤ እና ከወሊሶ ማረሚያ ቤቶች በደቡብ እና በኦሮሚያ ክልሎች አማካይነት በይቅርታ ከተለቀቁት መካከል አቶ ታግለን አወል፣ አቶ ናስር ሰይድ፣ አቶ ምላዙ ቲጃን፣ አቶ ደንበል መሐመድ፣ አቶ በድሩ ኡመር፣ አቶ ሚራጅ ሼህ ተማም፣ አቶ ዙመር ሁሴን፣ አቶ ጀማል ገረመው፣ አቶ አረብ ቆርቻ፣ አቶ ሙሀዲን አስፈር፣ አቶ ዝይን ቦንሳ ናቸው ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር አረጋግጠዋል።

የወለኔ ሕዝብ የራሱ ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ወግ ያለው ማህበረሰብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሕገመንግሥቱ ለሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች የተፈቀደው ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንዲረጋገጥለት አሁንም ሠላማዊ ትግሉን መቀጠሉን አቶ አብዲ ጠቁመዋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
218 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 926 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us