የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ተቋም፤ ለፖለቲካው ወገንተኛ አይሆንም

Wednesday, 20 June 2018 12:48

የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከፖለቲካ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ እንደሚንቀሳቀስ አስታወቀ።

አዲስ የተሾሙት ዳይሬክተር ጄኔራል አደም መሀመድ እንደገለጹት፣ “ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ከአደጋ ለመጠበቅ በሚደረገዉ ጥረት ተቋሙ ተልኮዉን ሲፈጽም ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ ሊሆን ይገባዋል” ብለዋል።

ዳይሬክተር ጄነራል አደም መሀመድ አይዘው እንተናገሩት፣ ተቋሙ የግዳጁን አፈጻጸም ዉጤታማነት ከፍ ለማድረግ መንግስት በሰጠዉ አቅጣጫ መሰረት በተቋሙ ውስጥ የሪፎርም ስራ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

ጄኔራል ዳይሬክተሩ ለህዝብ የሚተጋ፣ የሚሰራ እንዲሁም የሀገር እና ህዝብ ጥቅም የሚያስከብርና የሚያስቀጥል ተቋሙ እንደሚሆንና መንግስት በጀመረው የለውጥ ጉዞ ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ከማገልገል አኳያና የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት ብቃት ያለው ተቋም እንደሚደረግ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።

ትላንትና ዳይሬክተር ጄኔራሉን ጨምሮ አዲሱ የተቋሙ አዲስ አመራር ከሰራተኞች እና ባለሙያዎች ጋር ትውውቅ ማድረጋቸው ታውቋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
226 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1067 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us