በታራሚዎች ላይ ጉዳት ባደረሱ አካላት ላይ ምርመራ ሊካሄድ ነው

Wednesday, 20 June 2018 12:49

በማረሚያ ቤቶች በታራሚዎች ላይ የአካልና የሞራል ጉዳት ባደረሱ አካላት ላይ ምርመራ ሊካሄድ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል።

 

እንደ ጠቅላይ አቃቤ ህግ መረጃ ከሆነ በማረሚያ ቤቶች ውስጥ በታራሚዎች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሟል የሚሉ ተደጋጋሚ አቤቱታዎች እየተሰሙ መምጣታቸውን ተከትሎ በምን ሁኔታ በታራሚዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የሚያጣራ ኮሚቴ ተዋቅሮ የሚያጣራበት ሂደት እንደሚኖር ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ አመልክተዋል።

 

በርካታ ተጠርጣሪዎች ከዚህ ቀደም ከተያዙ በኋላ የማስረጃ ስብሰባና የማጣራት ሥራ ሲካሄድባቸው ከመቆየቱ ጋር በተያያዘ በርካቶች ከፍርድ በፊት ረዥም የእስር ጊዜን ለማሳለፍ የተገደዱ ሲሆን እንደ አቶ ብርሃኑ ገለፃ ከዚህ በኋላ ተጠርጣሪዎችን አጣርቶ መያዝ እንጂ ይዞ የማጣራት ሥራ አይከናወንም።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፈው ሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነበራቸው የጥያቄና መልስ ማብራሪያ ወቅት “ህገ መንግስቱ ጨለማ ቤት አስቀምጣችሁ ግረፉ፣ አሰቃዩ አይልም፤ አሸባሪ እኛ ነን በማለት ከተጠርጣሪዎችና ከታራሚዎች አያያዝ ጋር ያለውን ችግር ለማሳየት ሞክረዋል። የሰብአዊ መብት ጥሰቱም እስከ ወረዳ ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለፃቸው ይታወሳል። በተለይ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ማረሚያ ቤት የገቡ ዜጎች በምርመራ ወቅት ተደብድበናል፣ ጥፍራችን ተነቅሏል፣ ሞራል የሚነካ ስድብ ተሰድበናል፣ ፆታዊ ክብራችን ተገፏል የሚሉትንና የመሳሰሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ሲናገሩ ተሰምተዋል። አንዳንዶቹም መፅሐፍ በማሳተም ደረሰብን ያሉትን ግፍ ገልጸዋል። ጉዳዩ በተደጋጋሚ የሚነሳ ቢሆንም እስከ ዛሬም ድረስ እንዲጣራ የተደረገበት ሁኔታ አልነበረም።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
359 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1098 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us