የሬይንቦ እና የትራንስ ኔሽን የሔሊኮፕተር ማስጎብኘት አገልግሎት ይፋ ሆነ

Wednesday, 27 June 2018 12:51

 

ሬይንቦ የመኪና ኪራይና የአስጎብኚ አገልግሎት ኃ/የተ/የግል ኩባንያ እና ትራንስ ኔሽን ኤርዌስ በሔሊኮፕተር የማስጎብኘት አገልግሎት መጀመራቸውን ይፋ አደረጉ።

ሰኔ 17 ቀን 2010 ዓ.ም ኩባያዎቹ የአገልግሎቱን መጀመር በማስመልከት ለአስጎብኚና አራት የቱሪዝም ድርጅቶች ድርጅቶችን በመጋበዝ ስለፕሮግራሙ ገለጻ ከማድረጋቸውም ባሻገር በሔሊኮፕተር ወንጪ ሐይቅና አካባቢውን የማስጎብኘት ፕሮግራም አካሂደዋል።

አቶ ታፈሰ ሳህሌ የሬይንቦ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ስለፕሮግራሙ በሰጡት አጭር ማብራሪያ ሬይንቦ እና ትራንስ ኔሽን በመተባበር የሒሊኮፕተር ሳፋሪ የሚባለውን የቱሪስቶች ፍላጎት መሠረት በማድረግ ከአየር ላይ ወደምድር ቀረብ ብሎ የቱሪዝም ቦታዎችን፣ ከተሞችን የማስጎብኘት አገልግሎት መጀመራቸውን ለማብሰር የተዘጋጀ ነው ብለዋል። በሒሊኮፕተር ማስጎብኘት አገልግሎት ለአገራችን እምብዛም ያልተለመደ ነገር ቢሆንም በጎረቤት አገራት ኬንያን ጨምሮ በመላው ዓለም በስፋት የተለመደና አንድ ቱሪዝም የገቢ ምንጭ መሆኑን አስታውሰዋል። ይህ የጉብኝት ፕሮግራም በኢትዮጵያ ደረጃ እንዲስፋፋ በማሰብ ለመጀመሪያ ጊዜ 10 የአስጎብኚ ድርጅቶችን በመምረጥ በሁለት ዙር ከአዲስአበባ በቅርብ ርቀት የሚገኙ የጉብኝት ቦታዎችን ለማሳየት በማቀድ ለመጀመሪያ ዙር ሬይንቦን ጨምሮ አምስት አስጎብኚ ተቋማት መጋበዛቸውን ጠቅሰዋል። በሁለተኛ ዙርም ሌሎች አምስት ተቋማት እንደሚጋበዙ ጠቁመዋል።

የቤተሰባዊ ጉዞ ዓላማውም አስጎብኚ ድርጅቶች የሔሊኮፕተር ማስጎብኘት ፕሮግራም መኖሩን አውቀው በራሳቸው ፕሮግራሞች ውስጥ በማካተት አብሮ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታ እንዲፈጠር ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል።

በዕለቱ በወንጪ አካባቢ የሔሊኮፕተር ጉብኝት የተካሄደ ሲሆን በምዕራብ ሸዋ ደንዲ ወረዳ ሱሉ ቀበሌ የምትገኘዋን ከ100 ዓመት በላይ ያስቆጠረች የማርያም ቤተክርስቲያን በእንግዶቹ ተጎብኝቷል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
198 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 981 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us