ፕሮፌሰር መድሃኔ፣ የኢትዮ-ኤርትራ ድርድር በመተማመኛ ሰነዶች ልውውጥ እንዲጀመር አሳሰቡ

Wednesday, 27 June 2018 13:06

 

ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሰ በኢትዮጵያ መንግሥትና በኤርትራ መካከል የሚጀመረው የንግግር ምዕራፍ ወደ ዝርዝር ጉዳዮች በቀጥታ ከመግባታቸው በፊት በመተማመኛ ሰነዶች በመፈራረም ቢጀምሩት የበለጠ ውጤታማ ይሆናል አሉ።

በለንደን ኪንግስ ኮሌጅ የፀጥታና ደህንነት ዓለም ዓቀፍ ተመራማሪና መምህር ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሰ እንደሚሉት፣ በሁለቱ ሀገሮች ከትርምስ ነፃ የሚያደርጋቸውን ሂደት ያቀፈ ስምምነት (Anti destabilization Act) በመጀመሪያ መፈራረም አለባቸው። ይህም ሲባል፣ ከጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ውስጥ መውጣት፤ የትንኮሳ ተግባራት ማቆም፤ ነፍጥ ላነሱ ኃይሎች ከለላ ሁለቱም ሀገሮች ከመስጠት መቆጠብ፤ እንዲሁም የእስረኞች ልውውጥ ማድረግ መቅደም አለበት።

በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ መሆኑ ጠቀሜታው፤ ወደዝርዝር ጉዳዮች ከመዝለቃቸው በፊት ሁለቱም ሀገሮች የጥሞና ጊዜ ያገኛሉ። በሁለቱም ሀገሮች መካከል በርግጥ ወደ ሰላም ለመምጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት የመፈተሽና የማረጋገጥ እድል ያገኛሉ ብለዋል ፕሮፌሰር መድሃኔ።

 

(ሙሉ ቃለ-ምልልሱን በፖለቲካ ገጽ ይመልከቱ)¾

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
573 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 893 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us