5ሺ አባወራዎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ ለሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች የመሰረት ድንጋይ ተጣለ

Wednesday, 04 July 2018 12:42

-    አጠቃላይ የፕሮጀክቶቹ ወጪ 500 ሚሊዮን ብር ይጠጋል

 

በአዲስ አበባ ዙሪያ በልማት ምክንያት የተነሱ ከ5ሺ በላይ አርሶ አደሮች እና ከ32 ሺ በላይ ቤተሰቦቻቸውን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

ሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቶ ድሪባ ኩማ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በጋራ በመሆን የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጠውታል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ለማ መገርሳ በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት እንዳስቀመጡት፣ "መሬቱን ለልማት ያዋለ አርሶ አደር መኖሪያ ቤትና መስሪያ ቦታ ሊቸገር አይገባዉም" ሲሉ የፕሮጀክቱን አስፈላጊነትና ፍትሃዊነት አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ከተማ በበኩላቸው፣ አስተዳደሩ ባለፉት አምስት አመታት የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው፤ የልማት ፕሮጀክቶቹ በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ፣ አቃቂ በየካ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ኮልፌ ክፍለ ከተሞች ላይ ግንባታቸው እንደሚከናወኑ ተገልፆል።

በተያያዘም፣ ለአርሶአደሮቹ የተቀረጹት ፕሮጀክቶች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ታሳቢ የተደረጉ የሥራ ዘርፎቹ ሲሆኑ፣ እነሱም በከብትና የዶሮ እርባታ፣ የከብት ማድለብ፣ የወተት ሃብት ልማት ማቀነባበር እንዲሁም በአነስተኛ ንግድና ህንጻ በማከራየት ተጠቃሚ የሚሆኑበት ነው።

በተጓዳኝም፣ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ የውሃ፣ መንገድና የመብራት አገልግሎት የሚሰጡ ማህበራዊ ተቋማትም በፕሮጀክቱ ተካተዋል። በተጨማሪም የተለያዩ ሰርቶ ማሳያዎችን ጨምሮ የንግድ ማዕከላትና የመኖሪያ ቤት ግንባታም የሚከናወን መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

የልማት ፕሮጀክቶቹ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁ ሲሆን፣ ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ ግብዓቶችን ለማሟላት የጨረታ ሂደቱ ተጠናቋል። ከመስተዳድሩ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳው፣ ለልማት ፕሮጀክቶቹ የተለያዩ ግዥዎች ወጪ እስካሁን በ200 ሚሊየን ብር ተደርጓል። በቀጣይ ደግሞ 500 ሚሊየን ብር ለፕሮጀክቱ ግንባታ ማስፈጸሚያ ወጪ ይደረጋል ተብሏል።

እንዲሁም፣ በዕለቱ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ስሙ የካ አባዶ ፕሮጀክት 13 ለልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የአፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ለማስጀመር የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

በተያያዘም፣ የከተማ አስተዳደሩ ለ2 ሺህ 87 አርሶ አደሮች አሁን ላይ ወደ 52 ሚሊየን ብር በመመደብ የእለት ምግብና ተያያዥ ድጋፎች እያደረገ ይገኛል።

በዕለቱ ዝግጅት፣ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች፣ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ መንገሻ፣ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮችና በየደረጃው የሚገኙ የስራ ሀላፊዎች፣ የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች  እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

በአዲስ አበባ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የልማት አስተዳደር ተነሽ አርሶ አደሮች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ከመገለፁም በላይ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ዝርዝር መረጃ በመሰብሰብ፣ የውጭ ሀገሮችን ተሞክሮ በመደመር፣ እና የሕግ ማዕቀፍ በማበጀት ወደ ተግባራዊ ሥራዎች ገብቷል።¾  

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
144 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 940 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us