የ2ኛው ዙር የሆሄ ሥነጽሑፍ ሽልማት የመጨረሻ ዕጩ ምርጥ መጻሕፍት ታወቁ

Wednesday, 25 July 2018 13:17

ኖርዝ ኢስት ኤቨንትስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጄንሲ ጋር በመተባበር ዘንድሮ ለ2ኛ ጊዜ ያዘጋጀው የሆሄ የሥነጽሑፍ ሽልማት የ2009 ዓ.ም. ምርጥ መጻህፍት ዕጩዎች ይፋ ሆነዋል። የሽልማት ዝግጅቱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ የሥነ ጽሑፍ ምሁራን፣ ታዋቂ ደራሲያን እንዲሁም የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች የተውጣጣ የዳኞች ኮሜቴ በማዋቀር ለውድድሩ የተመዘገቡ መጻሕፍትን ሲገመግም ለሶስት ወራት ቆይታ አድርጓል።

 

በዚህ ዓመት የሆሄ ሽልማት በ2009 ዓ.ም የታተሙ በረጅም ልብ ወለድ ዘርፍ 19 መጻሕፍት፣ በልጆች መጻሕፍት ዘርፍ 17 እንዲሁም በግጥም መጻሕፍት ዘርፍ 24 መጻሕፍት ለውድድር ተመዝግበው ከእያንዳንዱ ምድብ 5 ምርጥ መጻሕፍትን ለመለየት በዳኞች ጥልቅ ግምገማ ሲካሄድ ቆይቷል።


በዚህም መሰረት በረጅም ልብ ወለድ ዘርፍ የሚከተሉት መጻሕፍት ምርጥ 5 መጻሕፍት ተብለው ተመርጠዋል።

 

 

Ø ስማርድ- በንጉሴ መኮንን
Ø አለመኖር - በዳዊት ወንድማገኝ (ዶ/ር)
Ø ጌርሳም - በዘርዓ ሰብሣጌጥ
Ø ዘርቆርጣሚው - በአለማየሁ በላይ
Ø በፍቅር ስም - በአለማየሁ ገላጋይ

በግጥም መጻሕፍት ዘርፍ የሚከተሉት አምስት መጻሕፍት በዕጩነት የተመረጡ ናቸው።

Ø የተገለጡ አይኖች - ሰለሞን ሞገስ
Ø የማለዳ ድባብ - በዕውቀቱ ስዩም
Ø ከሴተኛ አዳሪ የተኮረጀ ሳቅ- በላይ በቀለ ወያ
Ø የሀገሬ ንቅሳት - ሙሉዓለም ተገኘ ወርቅ
Ø ነፋስያነሳው ጥላ - ብርሀነስላሴ ከበደ

 

በልጆች መጻሕፍት ዘርፍ የምድቡ ዳኞች 5 መጻሕፍትን የመረጡ ሲሆን መጻሕፍቱም የሚከተሉት ናቸው።

 

Ø ቴዎድሮስ ፡ኡጋዝመሐመድ - በዳንኤል ወርቁ
Ø አባባ ትልቁና ሌሎች ትምህርታዊ ተረቶች- በየሺመቤት ካሳ
Ø አሻንጉሊቴ - በዓለም እሸቱ
Ø የጎመጀ ጅብ - በዓለም እሸቱ
Ø ልዋም - በሠማላዊትሐጎስ

 

ከየዘርፉ አንደኛ የሚወጡትን የመጨረሻዎቹን አሸናፊዎች ለመለየት በዳኞች ከሚደረገው ዳግም ግምገማ በተጨማሪ ከአንባቢያን የሚሰበሰበው ድምጽ ከአጠቃላይ ውጤቱ 20 በመቶ የሚይዝ ሲሆን አንባቢያን በአጭር የጽሁፍ መልዕክት 8240 ላይ ha የሚለውን ኮድ በማስቀደም አሸናፊ መሆን ይገባዋል የሚሉትን መጽሐፍ ርዕስ እስከነ ሐሴ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ መላክ ይችላሉ።


የሽልማት ፕሮግራሙ ነሐሴ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ከምሽቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴያትር ይካሄዳል። በሽልማቱ ላይ ከመጻሕፍቱ በተጨማሪ ለሥነጽሑፍ እድገት እና ለንባብ ባህል መዳበር የላቀ አስተዋጽ ኦያበረከቱ ግለሰቦች እና ተቋማት እውቅና ይሰጣቸዋል። የሽልማት ዝግጅቱ በኢቢኤስ ቴሌቭዥን በኢትዮጵያ እና በመላው አለም ላሉ ተመልካቾች የሚተላለፍ ይሆናል።


ከሽልማቱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት የሽልማቱን የፌስቡክ ገጽ www.facebook.com/Hohe-Awards እንዲሁም በሽልማቱ የትዊተር አድራሻ @HoheAwards መከታተል ይቻላል።


ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ በተካሄደው የመጀመሪያው የሆሄ የሥነጽሑፍ ሽልማት የአዳም ረታ የስንብት ቀለማት በረጅም ልብ ወለድ፣ የአበረ አያሌው ፍርድ እና እርድ በግጥም እንዲሁም የአስረስ በቀለ የቤዛቡችላ በልጆች መጻሕፍት ዘርፍ አሸናፊ እንደነበሩ ይታወቃል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1057 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 979 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us