ሚሊዮን ማቲዎስ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ

Wednesday, 25 July 2018 13:24

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በትላንትናው ዕለት መረጠ።

 

የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ለሌላ ኃላፊነት በመታጨታቸው ነው ተብሏል።


አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ቀደም ሲል የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ፣ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ የመንገድና ትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።


አቶ ሚሊዮን ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ የተጓደሉ የመስተዳድር ምክር ቤት እጩ አባላትን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል። በዚሁ መሠረት አቶ ኤሊያስ ሽኩር የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ መንድሙ ገብሬ የጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲሾሙላቸው ለምክር ቤቱ አቅርበው ሹመታቸውን አስፀድቀዋል።


አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በቅርቡ ክልሉን የሚያስተዳድረው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን/ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1842 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 903 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us