የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲኖዶሶች በአንድ ሲኖዶስ ለመመራት መስማማታቸው ተጠቆመ

Wednesday, 25 July 2018 13:27

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል የነበረው ልዩነት በዕርቀ ሰላም ወደ አንድነት ተመለሰ።

 

ባለፉት 27 ዓመታት በሁለት ሲኖዶሶች ስትመራ የቆየችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርሲቲያን ወደ አንድ ለማምጣት የሰላምና የእርቅ ጉባዔው በዋሸንግተን ደብረ ሀይል ቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስቲያን ባለፈው እሁድ የሁለቱም ልኡካን አባቶች በተገኙበት የጋራ ጸሎትና የመክፈቻ መርሐ ግብር ተጀምሯል።


ሲኖዶሶቹ ለሁለት በመከፈላቸው ምክንያት ችግር ላይ የነበሩ የእምነቱን ተከታዮች ወደ አንድነት ለማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ውይይት በማድረግ ወደ አንድነት ለመመለስ መስማማታውን የሰንደቅ ምጮች አስታውቀዋል። እንዲሁም በተጨማሪም "የሀገር ቤት ሲኖዶስ" እና "ስደተኛ ሲኖዶስ" የሚባለውን ለማስቀረት ተስማምተዋል።


በቅርቡ ወደ አሜሪካ ያቀኑትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸማጋይ ኮሚቴ አባላትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፅህፈት ቤታቸው ማነጋገራቸው የሚታወስ ነው።


ይህ የሰላምና የእርቅ ጉባዔ እስከ አርብ ድረስ የሚቆይ እንደሆነና በውይይቱ መጨረሻ መግላጫ እንደሚሰጥ ነው የተገለፀው።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
2020 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 939 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us