ብሔራዊ መለዮን ለመቀየር ባለሀብቶች ቃላቸውን ቢጠብቁ….?

Wednesday, 14 March 2018 13:32

 

አዲሱን የሀገሪቷን የልማት ብሔራዊ መለዮ (Nation branding) የለውጥ ስያሜ ከሚያሳኩት መካከል አንዱ የታላቁ ሕዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ነው፤ ግንባታው ከተጀመረ ሰባተኛ ዓመት ሆኖታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለባለሃብቶች የኮንፈረንስ እና የጉብኝት ፕሮግራም ሰሞኑን አዘጋጅቷል፡፡ ጽ/ቤቱ በያዘው እቅድ መሠረት ከመጋቢት 01 እስከ 03 ቀን 2010 ዓ.ም. ከባለሃብቶቹ ጋር የሕዳሴውን የሃይል ማመንጫ ግድብ ጉብኝት አድርገናል፡፡


ባለሃብቶች ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ ግንባታ 3 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ለመስጠት ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ሆኖም ባለሃብቶቹ ቃል ከገቡት የገንዘብ መጠን ውስጥ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ብቻ ክፍያ ፈጽመዋል፡፡ በመቶኛ ሲሰላም፣ አርባ ሁለት በመቶ ብቻ ነው፡፡


በአንፃሩ፤ የመንግስት ሠራተኞች ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ለማዋጣት ቃል የገቡት 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ቢሆንም፣ ቃል ከገቡት በላይ 4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ክፍያ ፈፅመዋል፡፡ ይሄም ሲባል ከቃላቸው በላይ የግማሽ ሚሊዮን ብር (500,000) ክፍያ ፈጽመዋል፡፡ ለሰባተኛ ጊዜም ክፍያ ለመፈጸም ተዘጋጅተዋል፡፡


ማስተባበሪያው ጉብኝቱን ያዘጋጀበት ዋና ዓላማም፣ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ለባለሃብቶቹ በማሳየትና በማሳወቅ የገቡትን ቃል በቁርጠኝነት ወደ ተግባር እንዲያወርዱት፤ አቅም እንዲሆናቸው ነው፡፡ ባለሃብቶቹም የግድቡ የግንባታ ደረጃ ከሚያስቡት ከሚጠብቁት በላይ መሆኑን በሥፍራው ተናግረዋል፡፡


የፕሮጀክቱ ዋና ሥራአስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ የባለሃብቶቹን ጉብኝት አስመልክተው እንደተናገሩት፣ “እኛን ለመጎብኘት አስቸጋሪ መንገድ አቋርጣቹህ መምጣታችሁ ለእኛ ትልቅ የሥራ አቅም ነው፡፡ ግድቡ ከኢኮኖሚ ጠቀሜታው በላይ አንድ ቤተሰብ አድርጎናል፡፡ ከሁሉም በላይ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የግድቡን ግንባታ ሥራ እንችላለን ብለን መጀመራችን ነው፡፡ ዛሬ ላይ ደግሞ ተያይዘን እንደጀመርነው፤ እንጨርሰዋለን፡፡ ያደረጋችሁት ድጋፍ ትክክለኛነት በጉብኝቱ ታረጋግጣላችሁ፡፡”


አያይዘውም፣ “እንደሕዝብ፣ እንደመንግስት፣ ከጎረቤቶቻችን ጋር በጋራ የመልማት ፖሊሲ ይዘን እየሰራን ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የአካባቢውን ሀገሮች እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህንን ፖሊሲያችን ደጋግመን እያስረዳን ነው የምንገኘው” ብለዋል፡፡

 

ስዕላዊ መግለጫ

የኮርቻ ቅርፅ ያለው ግድብ (Saddle Dam)

ይህ የሳድል ግድብ 50 ሜትር ከፍታ እና 5 ነጥብ 2 ኪ. ሜትር ይረዝማል፡፡ የግድቡ የሙሌት መጠን 15 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ነው፡፡ ለግድቡ የሙሌት ግብዓት አቅራቢያ ካለ የድንጋይ ኳሪ የተሞላ ነው፡፡

 

የከርሰምድር ፍተሸ ሥራዎች በተገቢው መልኩ ተከናውኗል፡፡ የግራውቲንግ፣ ፕላስቲክ ዳያፍራም ዎል ካስቲንግ ያለው የውሃ ስርገትና ማስተላለፍን የሚከላከሉ እንዲሁም የኢንስፔክሽን ጋለሪ ግንባታ ሥራዎች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሆኗል፡፡

 

የኃይል ማስተላለፊያ መስመር

ከኃይል ማመንጫው የመነጨውን ኃይል ወደ ብሔራዊ የኃይል ትስስር ለማገናኘት የሚያስችል ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በደዴሳ - ሆለታ - አዲስ አበባ የሚደርስ 725 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ባለ 500 ኪ.ቮ. ባለ ሁለት ሰርኩዩት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ተጠናቋል።

 

ከዚህም በተጨማሪ 240 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ባለ 400 ኪ.ቮ. ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት እስከ በለስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ድረስ ተገንብቶ አገለግሎት እየሰጠ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜም ለፕሮጀክቱ ግንባታ የሚውል የኤሌክትሪክ ኃይል ከብሔራዊ የኃይል ስርጭት መረብ ማቅረብ ያስቻለ ሲሆን፤ ይኸው መስመር ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ኃይል ማመንጨት ሲጀምርም ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የኃይል ማስተላለፊያውን በማዞር አገልግሎት ይሰጣል።

 

ውሃ ማስተንፈሻዎች (Spillways)

በፕሮጀክቱ የሚፈጠረው ሰው-ሰራሽ ሐይቅ (Reservoir) የማጠራቀም ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ 640 ሜ (Full Supply Level) ነው። ይህንንም ተጨማሪ የውሃ መጠን ተቀብለው ከግድቡ በታች ለመልቀቅ የሚያስችሉ ከዋናው ግድብ ግራ በኩል መዝጊያ ያለው የውሃ ማስተንፈሻ (Gated Spillway)፤ በዋናው ግድብ መካከለኛ ክፍል (Low Block Emergency Spillway) እና በሳድል ግድብ በስተቀኝ በኩል የሚገኝ ውሃ ማስተንፈሻ (Emergency Spillway) ግንባታቸው ከዘጠና በመቶ በላይ ተጠናቋል።

 

የወንዙን አቅጣጫ በማስቀየር የተከናወኑ ሥራዎች

የወንዙ አቅጣጫ ለሁለተኛ ጊዜ በግድቡ ግራ በኩል በማዞር 2008 ዓ.ም በዳይቨርሽን ቦክስ ከልቨርት በኩል እንዲያልፍ ተደርጓል። በመሆኑም ቀድሞ ውሃው ይሄድበት የነበረውን ቻናል ለRCC የማዘጋጀትና የመሙላት ሥራዎች በመከናወን ላይ ሲገኙ በአሁኑ ሰዓትም ከባሕር ጠለል በላይ እስከ 514 ሜትር ከፍታ ድረስ ተሞልቷል። የዳይቨርሽን ከልቨርት የላይኛውና የታችኛው በሮች ተጠናቀው ወደ ሥራ ገብተዋል።

 

 

ተጨማሪ መረጃ

ግድቡየሚገኝበትቦታ፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከጉባ ከተማ 20 ኪ.ሜ. ርቀት አካባቢ ላይ ይገኛል።

 

ከአዲስ አበባ ወደ ፕሮጀክቱ የሚወስዱ አማራጭ መንገዶች

አማራጭ 1 ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምዕራብ ደብረ-ማርቆስ፣ እንጅባራ እና ቻግኒ ከተሞችን በማቋረጥ በ730 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል።

 

አማራጭ 2 ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ ነቀምትና አሶሳ ከተሞችን በማቋረጥ በ830 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል።

 

የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል፡ 6,450 ሜጋ ዋት፣

 

አማካይ የውሃ ፍሰት መጠን፡ 1,547 ኪዩቢክ ሜትር በሰከንድ፣

 

የውሃው መጠን ከፍታ፡ ከባህር ጠለል በላይ 640 ሜ. ከፍተኛ እና ከባህር ጠለል በላይ 590 ሜ. ዝቅተኛ፤

 

የዋናው ግድብ ከፍታ እና ርዝመት፡ 145 ሜ. ከፍታ፣ 1 ነጥብ 8 ኪ.ሜ. ርዝመት

 

የኮርቻ ቅርፅ ግድብ (Saddle Dam) ከፈታ እና ርዝመት፣ 50 ሜ. ከፍታ፣ 5 ነጥብ 2 ሜ. ርዝመት

 

ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚፈጠር ኃይል ስፋት፡ 1,874 ስኩየር ኪ.ሜ.

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1323 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 148 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us