መንግስት ለሕዝብ የገባውን የግልፅነት ተጠያቂነትና ታማኝነት ቃሉን ሊጠብቅ ይገባል!!

Thursday, 24 December 2015 11:25

 

በሀገራችን በተለያየ ጊዜ በሚከሰት የአየር ንብረት መዛባት፣ በተለይም በዝናብ እጥረትና መጥፋት ምክንያት ድርቅ እየተከሰተ እንደኖረ ይታወቃል። ይህ በተለያየ ጊዜና ወቅት የሚከሰተው ድርቅ ሕዝቡን ለስደት፣ ለርሃብ፣ ለበሽታና ለሞት ጭምር ሲዳርግ ቆይቷል። ከዚህም ውስጥ በ1965/66 ዓ.ም በአብዛኛው በሰሜንና በምስራቅ ኢትዮጵያ የተከሰተው እና በ1977 ዓ.ም በሰሜን፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛውና በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ ተከስቶ የነበረው ድርቅና ርሃብ በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶና ታሪካዊ ጠባሳ ጥሎ ያለፈ እንደነበረ ይታወቃል።

ከ1977 ዓ.ም በኋላም በተለያየ ጊዜያት ተደጋጋሚ ድርቅ የተከሰተ ቢሆንም በሕዝብና በመንግስት ርብርብና በውጪው ዓለም ድጋፍ ወደ ከፋ ደረጃ ሳይደርስና ሕዝብን ለጉዳት ሳያዳርግ ለመቆጣጠር የተቻለበት ሁኔታ ተስተውሏል። ዘንድሮ ግን በዓለም ላይ በተከሰተው የአየር ንብረት መዛባት (Elion) ምክንያት በሀገሪቱ የተከሰተው መጠነ ሰፊ ድርቅ በብዙ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ጉዳት በማስከተል ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ድርቁ ከተከሰተባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች መሸሽና መሰደድ የጀመሩበት ደረጃ ላይ ደርሷል። በድርቁ ምክንያት እየመጣ ባለው ርሃብ መንስኤ በተለያየ አካባቢዎች ሰዎችና በርካታ ቁጥር ያላቸው እንስሳት እየሞቱ መሆኑን እየተገለፀ ይገኛል።

ሀገሪቱ በዚህ አይነት በድርቅ አደጋና ችግር ውስጥ ባለችበት በአሁኑ ወቅት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፡-

$1·         የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ማስተር ፕላን መሻሻል የኦሮሚያ ክልል መሬትን ያለአግባብ በመውሰድ የታለመ ነው በሚል እየተካሄደ ያለውን የተማሪዎችና የተለያየ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንቅስቃሴ ለመግታት ከመንግስት ኃይሎች እየተወሰደ ባለው አፀፋዊ እርምጃ የሰዎች ሕይወት መጥፋት፣ በዚህም ምክንያት በመንግስት ኃይሎ፣ በዩኒቨርስቲና በኮሌጅ ተማሪዎችና በተለያየ ሕብረተሰብ ክፍሎች መሀከል የተፈጠረው ውጥረት፤

$1·         በጎንደር ከተማ ባለው እስር ቤት በተከሰተ አደጋ ምክንያት የጠፋው የሰው ሕይወትና በዚህ ምክንያት በሕዝቡና በመንግስት ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ውጥረት፤

$1·         ለበርካታ ዘመናትና ላለፉት አምስትና ስድስት መንግስታት ዘመን ሳይወሰንና ሳይካለል የኖረው የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበርን የማካለል ጉዳይ በአንድ ወር ውስጥ እንደሚጀምር በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን አማካይነት በድንገት መገለፁና የሀገራችን መንግስት ዝምታን መምረጡ በሕዝቡ ውስጥ ከዳር እስከ ዳር ብዥታን፣ ግርታንና ጥያቄ መፍጠሩና በድንበሩ አካባቢ ባለው ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ውጥረት፣ ፍርሃትና ሽብርን መፍጠሩ ከድርቁ ችግርና አደጋ ጋር ተዳምሮ ሀገሪቱን ወደ አለመረጋጋት እየወሰዳት ሲሆን ሁኔታው ደግሞ መላውን ሕዝብ በስጋት፣ በጭንቀትና በውጥረት ውስጥ እየጣለ ይገኛል።

ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ወቅት መንግሥት ስለድርቁና ስለርሃቡ ሁኔታም ሆነ በሀገሪቱ በተለያየ ምክንያት እየተፈጠረ ስላለው ችግርና ውጥረት ግልጽ ሆኖ ለሕዝብ ሊያሳውቅ ሲገባ ይህን ማድረግ አልፈለገም። በየቦታው ሕዝቡ መንግስት ፈጥኖ እንዲደርስና ከአደጋ እንዲታደግ ማድረግ እየተማጸነ ይገኛል። ድርቁ ወደ ርሃብ እየተሸጋገረ መሆኑ፣ ሰዎችና እንስሳት እየሞቱ መሆኑ በብዙ መንገድ እየተገለፀ ቢሆንም መንግስት ግን ርሃብ አልተከሰተም፤ ከቁጥጥሬ ውጪ አይደለም በማለት በመሸፋፈን ላይ ነው። ስለአዲስ አበባው ማስተር ፕላንና ስለተፈጠረው ውጥረት፣ ስለጎንደሩ የእሳት ቃጠሎና ስለጠፋው የእስረኞች ሕይወት፣ ስለኢትዮ ሱዳን ድንበር መካለልና በድንበሩ አካባቢ ስለሚኖሩ ዜጎቻችን ዕጣ ፈንታ፣ ድንበሩ ስለሚከለልበት ተጨባጭ ሁኔታ መንግስት ለሕዝብ በግልፅ ሊያቀርብ ይገባል። ነገር ግን መንግስት እየተፈጠረ ያለውን ችግር ለሕዝብ በግልፅ ከማሳወቅ ይልቅ መሸፋፈንና መደባበቅን መምረጡ መላውን ሕዝብ ለከፋ ችግር የሚዳርግ፣ ወገን ለወገኑ እንዳይደርስ፣ አንዱ አካባቢ ከሌላው አካባቢ ጋር እንዳይረዳዳ የሚያደርግ፣ እንዲሁም ሕዝቡ በመንግስት አሰራር ላይ እምነት እንዲያጣ እንዲማረር የሚያደርግ እየሆነ መጥቷል። ስለዚህ፡-

$11.  የድርቁ ሁኔታና የተጎጂው ሕዝብ ቁጥርና መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ስለሆነ መንግስት ሁኔታውን ለብቻዬ እወጣለሁ ብሎ አፍኖ መያዙን ትቶ ኃላፊነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ የችግሩን መጠንና እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለሕዝብ ያለምንም መሸፋፈንና መደባበቅ በግልጽና በይፋ እንዲያቀርብና እንዲያሳውቅ እንጠይቃለን።

$12.  መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በእርስ እንዲረዳዳና እንዲደጋገፍ በማድረግ ከተለያዩ የሕዝብ አደረጃጀቶች፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከእርዳታና ልማት ድርጅቶች የተውጣጣ ብሔራዊ የእርዳታ አሰባሳቢና አስተባባሪ ኮሚቴ በአስቸኳይ እንዲቋቋምና በድርቁ በተጎዳው የሕዝብ ክፍል እርዳታና ድጋፍ የማሰባሰብ ፕሮግራም እንዲካሔድ መንግስት ሁኔታውን እንዲያመቻች እንጠይቃለን።

$13.  በጎንደር ከተማ በእስረኞች ላይ የደረሰውን አደጋ መንስኤና የጉዳቱን መጠን፣ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ማስተር ፕላን ምክንያት በኦሮሚያ አካባቢ የተፈጠረውን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ ሲባል በመንግስት ኃይሎች በተወሰደው እርምጃ በሰው ህይወት፣ አካልና ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት መጠን የሚያጣራና ለሕዝብ የሚያቀርብ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም እንጠይቃለን።

$14.  የኢትዮጵያና የሱዳንን ድንበር የማካለሉ ሂደት ከመካሔዱ በፊት መንግስት ከሕዝቡ ጋር በግልፅ እንዲያወያይና የማካለሉ ሁኔታ ለሕዝብ ግልጽ እንዲደረግ፣ እንዲሁም በድንበሩ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎቻችን ቀጣይ ዕጣ ፋንታና ዘላቂ ዋስትናን በሚመለከት ትክክለኛ ሁኔታ ለሕዝብ እንዲገለፅ እንጠይቃለን።

  ሰላም፣ ክብርና አንድነት ለኢትዮጵያ!!

የኢትዮጵያ ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

ህዳር 30 ቀን 2008 ዓ.ም

አዲስ አበባ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
554 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 69 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us