የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባህል ማዕከልና ሚዲያው ምንና ምን ናቸው?

Wednesday, 30 December 2015 14:01

 

 

ከስናፍቅሽ አዲስ

ባለፈው የሰንደቅ ጋዜጣ ዕትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባህል ማዕከልን የተመለከተ ጽሑፍ አነበብን፤ ጸሐፊው የማዕከሉ ሰራተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። በእርግጥ ይህ ሁሉ ቅሬታ በዚህ አግባብ ተቆጥሮ ልንዘረዝረው ባንችልም ብዙዎቻችን ይህንን በወፍ በረር ስንሰማው ኖረናል። አንዳንዶቹ ውስጣዊ አሰራሮች ስለሆኑ ባናውቃቸውም ብዙዎቹ ግን ጸሐይ የሞቃቸው እውነታዎች ናቸው። እኔን ቅር ያሰኘኝ ይሄን ያክል ምሬት የተሰማው ሰራተኛ አለ ያለውን ብልሹ አሰራርና የመልካም አስተዳደር ችግር በጽናት ሊታገል ያልቻለው ለምን ይሆን?

ወደ ዋናው ነጥቤ ልመለስ፤ ጸሐፊው ቅሬታቸውን ከሰነዘሩባቸው ሰዎች መካከል መገናኛ ብዙሃን አንዱ ናቸው። መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማእከል ፍትሕ ያጣ ተቋም ሲሆን ስለምን አልጮሃችሁም የሚል ወቀሳ ቀርቧል። በእርግጥ እናንተስ በተቋማችሁ ውስጥ ወዳጅና ጠላት ሚዲያዎች እየተባሉ ተቋማት በዓይን ቀለም ሲፈረጁ ከንፈር ከመምጠጥ ውጪ ታግላችኋል?!

ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ መግለጫ ሲሰጡ የግል የመንግስት ሚዲያ የማይሉትን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል ሚዲያ እየፈረጀ በዋና ዳይሬክተሩ “ደጄን እንዳይረግጡ” የተባሉ የሚዲያ ተቋማት የሉም? ይሄ ሀሰት አይደለም። የመንግስት ኮሙኒኬሽን የሚዲያ ጥቆማ መረጃዎችን ተመልከቱ፤ አንድም የብሔራዊ የባህል ማዕከል የሚዲያ ጥቆማ አለ? በዚህ አግባብ ከሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት ለመረጃ ዝጉ ተቋምስ ይሄ ተቋም ብቻ አይደለም? ይሄ ውሸት ከሆነ አሁኑኑ ወደ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጎራ ብሎ ማጣራት ይቻላል። መንግስት ኮሙኒኬሽን የሚልካቸውን የጥቆማ ኢሜይሎችንም ማየት ይቻላል፤ ታዲያ ይሄ ተቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ብለን እንዴት ልንታገለው እንችላለን።

መንግስት መዋቅሩን በየደረጃው እየፈተሸ ብልሹ አሰራርን እየታገለ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ስፖንሰር በሚል ሽፋን እየተመረጠ ገንዘብ በመስጠት፣ የፕሮፖጋንዳ ስራ ይሰራል እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማእከል አሰራሩን በተመለከተ አንድ ቀን ሀገራዊ የሆነ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ያውቃል?

ይሄንን መጻፍ ስለዚህ ማውራት ለሴክተሩ ስለማይጠቅም ዝም ብለናል፤ ይህ ማለት ብልሹ አሰራሩን ተቀብለናል ማለት አይደለም። ለምሳሌ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህል ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጥቆማችንን አቅርበናል። በተደጋጋሚ መታገሉን ለጠሉት ለቀድሞ ሚኒስትሮች ችግሩን አቅርበናል፤ ግን መልስ አለ?

በዚህ ሁኔታ ውስጥም ሆነን ተወቃሽ ሚዲያዎች ሆነናል። ያገነገነ ብልሹ አሰራርን ከዚህ በላይ ማስጮህ መልካም ነገር የምንሰራበትን ጊዜ ማባከን ስለሆነ የሚመራኝ መንግስት መርህ ገብቶኛል ያለ ቆራጥ አመራር ይታገለው። ወደ ተበደሉት ጣት መቀሰር ለማንም አይበጅም፤

እኔን ግን አሁንም የሚገርመኝ አንድ ነገር ይሄ አቋም የጥቂት ግለሰቦች አይደለም። እንደ ጋዜጠኛ የተቋሙን ሰራተኞች ባነጋገርኩበት ወቅት ሁሉ የሁሉም እንባና ብሶት ነው። አንዳንዶች ኢህአዴግ የለም ሌሎች ብልሹ አሰራር ያሸንፋል ብለው አምነው እንዲቀበሉ ተደርገዋል። በግምገማ ላይ ባነሱት ነጥብ ፍዳቸውን ያዩ ሰራተኞች ሲበደሉ ግምገማውን የመራው ሚኒስትር አልደረሰላቸውም። የሰማንውን ሁሉ ብንጽፍ የጻፍንው ለውጥ ካላመጣ ፍሬ ከርስኪ ነው። እናም እኛን አትውቀሱ…..¾

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
693 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1049 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us